መዝሙረ ዳዊት 138
138
ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ ፈተንኸኝ፥ ዐወቅኸኝም።
2አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ።
የልቤን ዐሳብ ሁሉ ከሩቁ ታስተውላለህ።
3ፍለጋዬንና መንገዴን አንተ ትመረምራለህ፤
መንገዶቼን ሁሉ አስቀድመህ ዐወቅህ፥
4የዐመፃ ቃል በአንደበቴ እንደሌለ።
5አቤቱ፥ አንተ እነሆ፥ የቀድሞውንና የኋላውን ሁሉ ዐወቅህ፤
አንተ ፈጠርኸኝ፥ እጅህንም በላዬ አደረግህ።
6ዕውቀትህ በእኔ ላይ ተደነቀች፤
በረታችብኝ፥ ወደ እርሷም ለመድረስ አልችልም።
7ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ?
ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?
8ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ፤
ወደ ጥልቁም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሲኦል” ይላል። ብወርድ፥ አንተ በዚያ አለህ፤
9እንደ ንስርም ክንፍን ብወስድ፥
እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥
10በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥
ቀኝህም ታኖረኛለች።
11በእውነት ጨለማ ይሸፍነኛል ብል፥
ሌሊት በደስታዬ ብርሃን ይሆናል፤
12ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና፥
ሌሊትም እንደ ቀን ታበራለችና፤
እንደ ጨለማዋ እንዲሁ ብርሃንዋ ነው።
13አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና፥
ከእናቴ ማኅፀን ጀምሮ ተቀበልኸኝ።#ግእዝ “ወተወከፍከኒ ከመ አእምር” ይላል።
14በመፈራት የተደነቅህ ነህና#ዕብ. “ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና” ይላል። አቤቱ፥ አመሰግንሃለሁ፤
ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ትረዳዋለች።
15በስውር የሠራኸው አጥንቴ ከአንተ አልተሰወረም፥
አካሌም ከምድር በታች፥
16ያልተሠራ አካሌንም#ግእዝ “ወዘሂ ገበርኩ ርእያ አዕይንቲከ” ይላል። ዐይኖችህ አዩ፤
ሁሉም በመጽሐፍህ ተጻፉ፥
በቀን ይፈጠራሉ፥
ነገር ግን ከእነርሱ አንድ ስንኳ አይኖርም።
17አቤቱ፥ ወዳጆችህ#ዕብ. “ዐሳቦችህ” ይላል። በእኔ ዘንድ እጅግ የከበሩ ናቸው፤
ከቀደምቶቻቸውም እጅግ ጸኑ።
18እቈጥራቸዋለሁ፥ ከአሸዋም ይልቅ ይበዛሉ፤
ተነሣሁ፥ ገናም ከአንተ ጋር ነኝ።
19አቤቱ፥ አንተ ኃጥኣንን የምትገድል ከሆንህስ፥
የደም ሰዎች ሆይ፥ ከእኔ ፈቀቅ በሉ።
20በዐሳባቸው ይኰራሉና፤
ከተሞችህንም በከንቱ ይወስዷቸዋል።
21አቤቱ፥ የሚጠሉህን እኔ የጠላሁ አይደለሁምን?
ስለ ጠላቶችህም አልጠፋሁምን?
22ፍጹም ጥልን ጠላኋቸው፥ ጠላቶችም ሆኑኝ።
23አቤቱ፥ መርምረኝ፥ ልቤንም ፈትን፤
ፈትነኝ፥ መንገዶችንም ዕወቅ፤
24በደልም በእኔ ላይ ቢገኝ እይ፤
የዘለዓለምንም መንገድ ምራኝ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 138: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ