የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 113

113
ሃሌ ሉያ።
1እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ፥
የያ​ዕ​ቆ​ብም ወገን ከጠ​ላት ሕዝብ በወጡ ጊዜ፥
2ይሁዳ መመ​ስ​ገ​ኛው፥
እስ​ራ​ኤ​ልም ግዛቱ ሆነ።
3ባሕር አየች፥ ሸሸ​ችም፥
ዮር​ዳ​ኖ​ስም ወደ​ኋ​ላው ተመ​ለሰ።
4ተራ​ሮች እንደ ኮር​ማ​ዎች፥
ኮረ​ብ​ቶ​ችም እንደ በጎች ጠቦ​ቶች ዘለሉ።
5አንቺ ባሕር የሸ​ሸሽ፥
አን​ተም ዮር​ዳ​ኖስ ወደ ኋላህ የተ​መ​ለ​ስህ፥ ምን ሁና​ችሁ ነው?
6እና​ን​ተም ተራ​ሮች፥ እንደ ኮር​ማ​ዎች፥
ኮረ​ብ​ቶ​ችስ፥ እንደ በጎች ጠቦ​ቶች ለምን ዘለ​ላ​ችሁ?
7ከያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ ፊት፥
ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ምድር ተና​ወ​ጠች፤
8ዐለ​ቱን ወደ ውኃ ምንጭ፥
ባል​ጭ​ቱ​ንም ወደ ውኃ ኩሬ የለ​ወጠ።
9 # በዕብ. መዝ. 115 ነው። ለእኛ አይ​ደ​ለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይ​ደ​ለም፥
ነገር ግን ለስ​ምህ፥
ስለ ምሕ​ረ​ት​ህና ስለ እው​ነ​ት​ህም ምስ​ጋ​ናን እን​ስጥ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ስጥ” ይላል።
10አሕ​ዛብ፥ “አም​ላ​ካ​ቸው ወዴት ነው?” አይ​በሉ።
11አም​ላ​ካ​ች​ንስ በላይ በሰ​ማይ ነው፤
በሰ​ማ​ይም በም​ድ​ርም፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር#“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ። የፈ​ቀ​ደ​ውን ሁሉ አደ​ረገ።
12የአ​ሕ​ዛብ ጣዖ​ታ​ቶች የወ​ር​ቅና የብር፥
የሰው እጅ ሥራ ናቸው።
13አፍ አላ​ቸው ግን አይ​ና​ገ​ሩም፤
ዐይን አላ​ቸው ግን አያ​ዩም፤
14ጆሮ አላ​ቸው ግን አይ​ሰ​ሙም፤
አፍ​ንጫ አላ​ቸው ግን አያ​ሸ​ት​ቱም፤
15እጅ አላ​ቸው ግን አይ​ዳ​ስ​ሱም፤
እግር አላ​ቸው ግን አይ​ሄ​ዱም፤
በጉ​ሮ​ሮ​አ​ቸ​ውም አይ​ና​ገ​ሩም።
16በአ​ፋ​ቸው ትን​ፋሽ የለም፥#“በአ​ፋ​ቸው ትን​ፋሽ የለም” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸ​ውም የሚ​ያ​ም​ኑ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ እንደ እነ​ርሱ ይሁኑ።
17የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኑ፤
ረዳ​ታ​ቸ​ውና መታ​መ​ኛ​ቸው እርሱ ነው።
18የአ​ሮን ወገ​ኖች ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኑ፤
ረዳ​ታ​ቸ​ውና መታ​መ​ኛ​ቸው እርሱ ነው።
19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈሩ ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኑ፤
ረዳ​ታ​ቸ​ውና መታ​መ​ኛ​ቸው እርሱ ነው።
20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አስ​በን ባር​ከ​ንም#ዕብ. “ዐሰ​በን ይባ​ር​ከ​ና​ልም” ይላል።
የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወገ​ኖች ባርክ፥ የአ​ሮ​ን​ንም ወገ​ኖች ባርክ።
21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩ​ትን፥
ትን​ን​ሾ​ች​ንና ትል​ል​ቆ​ችን ሁሉ ባር​ካ​ቸው።#ዕብ. “ይባ​ር​ካል” ይላል።
22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ​ያ​ችሁ፥
በላ​ያ​ች​ሁና በል​ጆ​ቻ​ችሁ ላይ ይጨ​ምር።
23እና​ንተ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ለሠራ
ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረ​ካ​ችሁ ናችሁ።
24የሰ​ማ​ዮች ሰማይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤
ምድ​ርን ግን ለሰው ልጆች ሰጠ።
25አቤቱ፥ ሙታን የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑህ አይ​ደ​ሉም፥
ወደ ሲኦ​ልም የሚ​ወ​ርዱ ሁሉ፤
26እኛ ሕያ​ዋን ግን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ሰ​ግ​ና​ለን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ