የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 109

109
የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1ጌታ ጌታ​ዬን፥ “ጠላ​ቶ​ች​ህን ለእ​ግ​ርህ መረ​ገጫ እስ​ካ​ደ​ር​ግ​ልህ ድረስ
በቀኜ ተቀ​መጥ” አለው።
2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኀ​ይ​ልን በትር ከጽ​ዮን ይል​ክ​ል​ሃል፤
በጠ​ላ​ቶ​ች​ህም መካ​ከል ትገ​ዛ​ለህ።
3ቀዳ​ማዊ፦ በኀ​ይል ቀን፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. በኀ​ይ​ልህ ቀን” ይላል።
በቅ​ዱ​ሳን ብር​ሃን ከአ​ንተ ጋር ነበር፥
ከአ​ጥ​ቢያ ኮከብ አስ​ቀ​ድሞ ከሆድ ወለ​ድ​ሁህ።
4እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት
አንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ካህን ነህ ብሎ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማለ አይ​ጸ​ጸ​ት​ምም።
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ኝህ ነው፥
ነገ​ሥ​ታ​ትን በቍ​ጣው ቀን ይቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋል።
6በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይፈ​ር​ዳል፥
ሬሳ​ዎ​ች​ንም ያበ​ዛል፤
በም​ድር ላይ የብ​ዙ​ዎ​ችን ራሶች ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል።
7በመ​ን​ገድ ከፈ​ሳሽ ውኃ ጠጡ፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ይጠ​ጣል” ይላል።
ስለ​ዚህ ራስ ከፍ ከፍ ይላል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ