መጽሐፈ ምሳሌ 4:20-26

መጽሐፈ ምሳሌ 4:20-26 አማ2000

ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ፤ ጆሮህንም ወደ ቃሌ አዘንብል። ምንጮችህ እንዳይደርቁ፥ በልብህ ጠብቃቸው። ለሚያገኙአቸው ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ናቸውና። ልብህን አጥብቀህ ጠብቅ፥ የሕይወት መገኛ ከእርሱ ነውና። ክፉ አፍን ከአንተ አርቅ፥ ሐሰተኞች ከንፈሮችንም ከአንተ አስወግድ። ዐይኖችህም አቅንተው ይዩ፥ ሽፋሽፍቶችህም ወደ እውነት ያመልክቱ። ለእግርህ ቀና መሄጃ ሥራ፥ መንገዶችህንም አቅና።