የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ምሳሌ 3:11-13

መጽሐፈ ምሳሌ 3:11-13 አማ2000

ልጄ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ ቸል አትበል፥ በመገሠጹም ከእርሱ የተነሣ አትመረር። አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ እግዚአብሔር የሚወድደውን ይገሥጻል፥ የሚቀበላቸውን ልጆቹን ይገርፋልና። ጥበብን የሚያገኝ፥ ማስተዋልንም የሚያውቅ መዋቲ ሰው ብፁዕ ነው።