የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ምሳሌ 14

14
1ብልሆች ሴቶች ቤቶችን ይሠራሉ፤
ሰነፎች ሴቶች ግን በእጃቸው ያፈርሳሉ።
2በቅንነት የሚሄድ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል፤
መንገዱን የሚያጣምም ግን ይናቃል።
3ከሰነፎች አፍ የስድብ በትር ይወጣል፤
የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።
4በሬዎች በሌሉበት ስፍራ በረቱ ንጹሕ ነው፤
ብዙ እህል ግን በበሬዎች ኀይል ይገኛል።
5የታመነ ምስክር አይዋሽም፤
የሐሰት ምስክር ግን ሐሰትን ያቀጣጥላል።
6በክፉዎች ዘንድ ጥበብን ትፈልጋለህ፥ አታገኛትምም፤
ዕውቀት ግን በብልሆች ዘንድ በቀላሉ ይገኛል።
7በሰነፍ ሰው ፊት ሁሉ ጠማማ ነው፥
የብልሆች ከንፈር ግን የዕውቀት ጋሻ ነው።
8የዐዋቂዎች ጥበብ መንገዳቸውን ታውቃለች፤
የሰነፎች ስንፍና ግን ወደ ስሕተት ይመራል።
9የኃጥኣን ቤቶች መንጻትን ይሻሉ፥
የጻድቃን ቤቶች ግን የተወደዱ ናቸው።
10የዐዋቂ ሰው ልብ ለሰውነቱ ኀዘን ነው፤
ደስ ባለውም ጊዜ ከጥል ጋር ግንኙነት የለውም።
11የክፉዎች ቤቶች ይፈርሳሉ፤
የቅኖች ማደሪያዎች ግን ይጸናሉ።
12በሰዎች ዘንድ ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤
ፍጻሜዋ ግን ወደ ሲኦል ጕድጓድ ታደርሳለች።
13ከደስታ ጋር ኀዘን አይቀላቀልም፥
የደስታ ፍጻሜ ግን ወደ ኀዘን ይመለሳል።
14ልበ ትዕቢተኛ ከራሱ መንገድ ይጠግባል።
ደግ ሰውም ከራሱ ዐሳብ ይጠግባል።
15የዋህ ነገርን ሁሉ ያምናል፤
ዐዋቂ ግን ወደ ንስሓ ይመለሳል።
16ብልህ ሰው ፈርቶ ከክፉ ይሸሻል፤
አላዋቂ ግን ራሱን ተማምኖ ከኃጥኣን ጋር አንድ ይሆናል።
17ቍጡ ሰው ያለምክር ይሠራል፤
ብልህ ግን ብዙ ይታገሣል።
18አላዋቂዎች ሰዎች ክፋትን ይካፈላሉ፤
ዐዋቂዎች ሰዎች ግን ማስተዋልን ፈጥነው ይይዟታል።
19ክፉዎች በደጎች ፊት ይሰነካከላሉ፥
ኃጥኣን ግን በጻድቃን በር ያገለግላሉ።
20ባለጠጎች ወዳጆች ድሆች ወዳጆችን ይጠላሉ፤
የባለጠጎች ወዳጆች ግን ብዙዎች ናቸው።
21ድሃውን የሚንቅ ኀጢአትን ይሠራል፤
ለድሃ የሚራራ ግን ብፁዕ ነው።
22ስሕተተኞች ክፉን ያስባሉ፤
ደጋጎች ግን ምሕረትንና እውነትን ያስባሉ።
ክፋትንም የሚሠሩ ምሕረትንና ይቅርታን አያውቁም።
ነገር ግን ታማኝነትና ቸርነት ደግ በሚሠሩ ዘንድ ናቸው።
23በሁሉ ነገር ጠንቃቃ ለሆነ ብዙ ትርፍ አለው።
ደስታን ፈላጊና ሰነፍ ግን ችግረኛ ነው።
24ዐዋቂ ሰው የጠቢባን ዘውድ ነው፤
የአላዋቂዎች ተግባር ግን ክፉ ነው።
25እውነተኛ ምስክር ነፍስን ከክፉ ያድናል፥
ሐሰተኛ ግን ሐሰትን ያቀጣጥላል።
26እግዚአብሔርን ለሚፈራ ጽኑዕ ተስፋ አለው፥
ለልጆቹም መጠጊያን ይተዋል።
27የእግዚአብሔር ትእዛዝ የሕይወት ምንጭ ነው።
ሰዎችንም ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጡ ያደርጋል።
28የንጉሥ ክብር በሕዝብ ብዛት ነው፤
የገዥ ውድቀት ግን በሕዝብ ማነስ ነው።
29ትዕግሥተኛ ሰው ጥበብ የበዛለት ይሆናል፤
ትዕግሥት የጐደለው ሰው ግን ሰነፍ ነው፤
30የሚያስታርቅ ሰው የልብ ፈዋሽ ነው፤
ቀናተኛ ልብ ግን ለአጥንት ነቀዝ ነው።
31ድሃን የሚያስጨንቅ ፈጣሪውን ያስቈጣዋል፤
ፈጣሪውን የሚያከብር ግን ለድሃ ምሕረትን ያደርጋል።
32ኃጥእ በክፋቱ ይወገዳል፤
በቸርነቱ የሚታመን ግን ጻድቅ ነው።
33በደግ ሰው ልብ ጥበብ ታድራለች፤
በአላዋቂ ሰው ልብ ግን አትታወቅም።
34ጽድቅ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤
ኀጢአት ግን ሕዝብን ታሳንሳለች።
35አስተዋይ መልእክተኛ በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ነው፤
በመልካም ጠባዩም ውርደትን ከራሱ ያርቃል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}