መጽሐፈ ምሳሌ 12:12-14

መጽሐፈ ምሳሌ 12:12-14 አማ2000

የኃጥኣን ምኞት ክፋት ናት። የጻድቃን ሥር ግን የጸና ነው። ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤ ጻድቅ ግን ከእርሱ ያመልጣል። አስፍቶ የሚመለከት ሰው ብዙ ምሕረትን ያገኛል። ድንገት በበር የሚገናኝ ግን ነፍሳትን ያስጨንቃል። የሰው ነፍስ ከአፉ ፍሬ መልካም ነገርን ትጠግባለች፥ ሰውም የከንፈሩን ዋጋ ይቀበላል።