መጽሐፈ ምሳሌ 11
11
1አባይ ሚዛን በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው፤
እውነተኛ ሚዛን ግን በእርሱ ዘንድ የተመረጠ ነው።
2ትዕቢት ባለበት በዚያ ውርደት አለ፤
የየዋሃን አፍ ግን ጥበብን ይማራል።
3ጻድቃንን ፍጻሜያቸው ትመራቸዋለች፤
ኃጥኣንን ግን መሰነካከላቸው ትማርካቸዋለች።
4በቍጣ ቀን ገንዘብ አይጠቅምም፤
ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች።
ጻድቅ በሞተ ጊዜ ጸጸትን ይተዋል፥
የኀጢአተኛ ሞት ግን በእጅ የተያዘና ሣቅ ይሆናል።
5የፍጹም ሰው ጽድቁ መንገዱን ያቀናለታል፤
ኀጢአት ግን በክፉዎች ላይ ትወርዳለች።
6ቅኖች ሰዎችን ጽድቃቸው ይታደጋቸዋል፤
ኃጥኣን ግን ባለማወቃቸው ይጠመዳሉ።
7ጻድቅ ሰው በሞተ ጊዜ ተስፋውን አያጣም፥
የክፉዎች ትምክሕታቸው ግን ትጠፋለች።
8ጻድቅ ከወጥመድ ያመልጣል፥
ኀጢአተኛ ግን በእርሱ ፋንታ ይሰጣል።
9በክፉዎች አፍ የሀገር ወጥመድ አለ፥
የጻድቃን ዕውቀት ግን መልካም ጎዳና ናት።
10በጻድቃን ደግነት ከተማ ትቀናለች፥
በክፉዎችም ጥፋት ደስ ይላታል።
11በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፤
በኃጥኣን አፍ ግን ትገለበጣለች።
12ጥበብ የጐደለው የሀገሩን ሰው ይንቃል።
ብልህ ሰው ግን ጸጥታን ያመጣል።
13ሁለት ምላስ የሆነ ሰው የጉባኤን ምሥጢር ይገልጣል፤
በአንደበቱ የታመነ ግን ነገርን ይሰውራል።
14መምህር የሌላቸው እንደ ቅጠል ይወድቃሉ።
በምክር ብዛት ግን ደኅንነት ይኖራል።
15ክፉ ሰው ከጻድቅ ጋር በተቀላቀለ ጊዜ ይከፋል፥
የሰላም ድምፅንም ይጠላል።
16ደግ ሴት ለባሏ ክብርን ታስገኛለች፥
ጽድቅን የምትጠላ ሴት ግን የውርደት ወንበር ናት።
ሐኬተኞች ከብልጽግና ይደኸያሉ፥
ብርቱዎች ግን ብልጽግናን ይከተላሉ።
17ቸር ሰው ለነፍሱ መልካም ያደርጋል፤
ጨካኝ ግን ሥጋውን ይጐዳል።
18ክፉ ሰው የበደልን ሥራ ይሠራል፤
ለጻድቃን ዘር ግን የታመነ ዋጋ አለው።
19ጻድቅ ልጅ ለሕይወት ይወለዳል፤
የኃጥኣን መወለድ ግን ለሞት ነው።
20ጠማማ መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤
በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን በፊቱ የተመረጡ ናቸው።
21በሐሰት እጅን በእጅ የሚመታ አይድንም፤
ጽድቅን የሚዘራ ግን የታመነ ዋጋን ያገኛል።
22የወርቅ ቀለበት በእርያ አፍንጫ እንደ ሆነ፥
የክፉ ሴትም ውበትWa እንዲሁ ነው።
23የጻድቃን ምኞት መልካም ነው፤
የኃጥኣን ተስፋ ግን ይጠፋል።
24የየራሳቸውን የሚዘሩና የሚያበዙ አሉ፤
እየሰበሰቡ የሚያጐድሉም አሉ።
25የተባረከች ሰውነት ሁሉ ትጠግባለች፥
ቍጡ ሰው ግን ክፉ ነው።
26ስንዴውን የሚያደልብ ለአሕዛብ ይተወዋል።
በረከት ግን በሚሰጥ ሰው ራስ ላይ ነው።
27መልካምን የሚያስብ መልካም ክብርን ይወድዳል።
ክፋትን የሚፈልግን ግን ክፋት ታገኘዋለች።
28በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፤
ጻድቃንን የሚቀበል ግን ይለመልማል።
29ቤቱን የማያውቅ ሰው ነፋስን ይወርሳል፥
ሰነፍም ለጠቢብ ተገዥ ይሆናል።
30ከጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ይወጣል።
የዐመፀኞች ነፍሳት ግን በድንገት ይወገዳሉ።
31እነሆ፥ ጻድቅ በምድር ላይ በጭንቅ የሚድን ከሆነ፥
ይልቁንስ ኃጥእና ዐመፀኛ በወዴት ይገለጣሉ?
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 11: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ