ጢሞቴዎስን እንድልክላችሁ፥ እኔም ዜናችሁን ሰምቼ ደስ እንዲለኝ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋ አደርጋለሁ። ከእርሱ በቀር፥ እንደ እኔ ሆኖ በማስተዋል ግዳጃችሁን የሚፈጽም የለኝምና። የክርስቶስን ያይደለ፥ ሁሉም የራሱን ጉዳይ ያስባልና። ልጅ አባቱን እንደሚያገለግል፥ በወንጌል ትምህርት እንደ አገለገለኝ፥ የዚህን ሰው ጠባዩን ታውቃላችሁ። እንግዲህ እንዴት እንደ አለሁ በዐወቅሁ ጊዜ፥ እርሱን በቶሎ እንደምልከው ተስፋ አደርጋለሁ፤ እኔም ፈጥኜ እንደምመጣ በጌታችን አምናለሁ። አሁንም አብሮኝ የሚሠራውን ወንድማችንን አፍሮዲጡን ወደ እናንተ ልልከው አስቤአለሁ፤ እርሱም የክርስቶስ ሎሌ ነው፤ ለእናንተም መምህራችሁ ነው፤ ለእኔም ለችግሬ ጊዜ መልእክተኛዬ ነው። እንደ ታመመ፥ ለሞትም እንደ ደረሰ መስማታችሁን ዐውቆ ሊያያችሁ ይሻልና። ነገር ግን እግዚአብሔር ማረው፤ በኀዘን ላይ ኀዘን እንዳይጨመርብኝ ለእኔም እንጂ ለእሱ ብቻ አይደለም። እንድታዩትና ደስ እንዲላችሁ፥ እኔም እንዳላዝን በቶሎ እልከዋለሁ። እንግዲህ በጌታችን በፍጹም ደስታ ተቀበሉት፤ እንደዚህ ያሉትንም ሁሉ አክብሩአቸው። የእግዚአብሔርን ሥራ ስለ መሥራት እስከ ሞት ደርሶአልና፥ ከእኔ መልእክትም እናንተ ያጐደላችሁትን ይፈጽም ዘንድ ሰውነቱን አሳልፎ ሰጥቶአልና።
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:19-30
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች