የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 4

4
የቀ​ዓት ልጆች ተግ​ባር
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ 2“ከሌዊ ልጆች መካ​ከል በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች የቀ​ዓ​ትን ልጆች ለዩ​አ​ቸው፤ 3ከሃያ አም​ስት#ዕብ. “ከሠ​ላሳ” ይላል። ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​በ​ትን ሁሉ ትለ​ያ​ለህ። 4በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሥራ ይህ ነው፤ 5ሰፈሩ በተ​ነሣ ጊዜ አሮ​ንና ልጆቹ ገብ​ተው የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን መጋ​ረጃ ያወ​ር​ዳሉ፤ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ታቦት ይጠ​ቀ​ል​ሉ​በ​ታል፤ 6በላ​ዩም የአ​ቆ​ስ​ጣ​ውን ቍር​በት መሸ​ፈኛ ያድ​ር​ጉ​በት፤ ከእ​ር​ሱም በላይ ሁለ​ን​ተ​ናው ሰማ​ያዊ የሆነ መጐ​ና​ጸ​ፊያ ያግ​ቡ​በት፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግ​ቡ​በት። 7በኅ​ብ​ስተ ገጹ ገበታ ላይም ሰማ​ያ​ዊ​ውን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ር​ጉ​በት፤ በእ​ር​ሱም ላይ ወጭ​ቶ​ቹን፥ ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽዋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ለማ​ፍ​ሰ​ስም መቅ​ጃ​ዎ​ቹን ያድ​ር​ጉ​በት፤ ሁል​ጊ​ዜም የሚ​ኖር ኅብ​ስት በእ​ርሱ ላይ ይሁን። 8በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ቀይ መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ርጉ፤ በአ​ቆ​ስ​ጣ​ውም ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይሸ​ፍ​ኑት። መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግቡ። 9ሰማ​ያ​ዊ​ው​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይው​ሰዱ፤ የሚ​ያ​በ​ሩ​ባ​ት​ንም መቅ​ረዝ፥ ቀን​ዲ​ሎ​ች​ዋ​ንም፥ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ የኵ​ስ​ታሪ ማድ​ረ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ እር​ስ​ዋ​ንም ለማ​ገ​ል​ገል የዘ​ይ​ቱን ማሰ​ሮ​ዎች ሁሉ ይሸ​ፍኑ፤ 10እር​ስ​ዋ​ንና ዕቃ​ዎ​ች​ዋን ሁሉ በአ​ቆ​ስጣ ቍር​በት መሸ​ፈኛ ውስጥ ያድ​ርጉ፤ በመ​ሸ​ከ​ሚ​ያ​ውም ላይ ያድ​ር​ጉት። 11በወ​ር​ቁም መሠ​ዊያ ላይ ሰማ​ያ​ዊ​ውን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ር​ጉ​በት፤ በአ​ቆ​ስ​ጣም ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይሸ​ፍ​ኑት፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግቡ። 12በመ​ቅ​ደ​ስም ውስጥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን የማ​ገ​ል​ገ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ ይው​ሰዱ፤ በሰ​ማ​ያ​ዊ​ዉም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ውስጥ ያስ​ቀ​ም​ጡት፤ በአ​ቆ​ስ​ጣም ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይሸ​ፍ​ኑት፤ በመ​ሸ​ከ​ሚ​ያ​ውም ላይ ያድ​ር​ጉት። 13አመ​ዱ​ንም ያስ​ወ​ግዱ፤ መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያድ​ርጉ፤ ሐም​ራ​ዊ​ዉ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ር​ጉ​በት፤ 14የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን ዕቃ​ውን ሁሉ፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹን፥ ሜን​ጦ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽዋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንም፥ መክ​ደ​ኛ​ዎ​ቹ​ንም፥ ያመድ ማፍ​ሰ​ሻ​ዎ​ቹን፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ያመድ ማፍ​ሰ​ሻ​ዎ​ችን” የሚ​ለ​ውን አይ​ጽ​ፉም። የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ ያስ​ቀ​ም​ጡ​በት፤ በእ​ር​ሱም የአ​ቆ​ስ​ጣን ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይዘ​ርጉ፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግቡ። ሐም​ራ​ዊ​ዉ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ወስ​ደው ማስ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ው​ንና ማስ​ቀ​መ​ጫ​ውን ይሸ​ፍ​ኑት፤ በአ​ቆ​ስ​ጣው ቍር​በት መሸ​ፈኛ ውስ​ጥም አድ​ር​ገው በመ​ሸ​ከ​ሚ​ያ​ዎቹ ላይ ያኑ​ሩት፤ 15አሮ​ንና ልጆቹ መቅ​ደ​ሱ​ንና የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍ​ነው ከጨ​ረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀ​ዓት ልጆች ሊሸ​ከ​ሙት ይገ​ባሉ። እን​ዳ​ይ​ሞቱ ግን ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን አይ​ንኩ። በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው። 16የካ​ህ​ኑም የአ​ሮን ልጅ አል​ዓ​ዛር በመ​ብ​ራቱ ዘይት በጣ​ፋ​ጩም ዕጣን ላይ ፥ ሁል​ጊ​ዜም በሚ​ቀ​ር​በው በእ​ህሉ ቍር​ባ​ንና በቅ​ባቱ ዘይት ላይ ሹም ነው፤ ድን​ኳ​ኑን ሁሉ፥ በእ​ር​ሱም ውስጥ ያለ​ውን ሁሉ፥ መቅ​ደ​ሱ​ንና ዕቃ​ውን ይጠ​ብ​ቃል።”
17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ 18“የቀ​ዓ​ትን ወገ​ኖች ነገድ ከሌ​ዋ​ው​ያን መካ​ከል አታ​ጥ​ፉ​አ​ቸው፤ 19ነገር ግን ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ በቀ​ረቡ ጊዜ በሕ​ይ​ወት ይኖሩ ዘንድ እንጂ እን​ዳ​ይ​ሞቱ እን​ዲሁ አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ አሮ​ንና ልጆቹ ይግቡ፤ 20ከእ​ነ​ርሱ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ሥራ​ው​ንና ሸክ​ሙን ያዘ​ጋጁ፤ ነገር ግን እን​ዳ​ይ​ሞቱ ንዋየ ቅዱ​ሳ​ቱን ለድ​ን​ገት እን​ኳን ለማ​የት አይ​ግቡ።”
የጌ​ድ​ሶን ልጆች ተግ​ባር
21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 22“የጌ​ድ​ሶ​ንን ልጆች ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ጀም​ረህ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ቍጠ​ራ​ቸው። 23የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት#ዕብ. “ሠላሳ” ይላል። ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠ​ራ​ቸው። 24የጌ​ድ​ሶን ወገ​ኖች ሥራ በማ​ገ​ል​ገ​ልና በመ​ሸ​ከም ይህ ነው፤ 25የድ​ን​ኳ​ኑን መጋ​ረ​ጃ​ዎች፥ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ውን፥ በላ​ዩም ያለ​ውን የአ​ቆ​ስ​ጣ​ውን ቍር​በት መደ​ረ​ቢያ፥ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም መጋ​ረጃ፥ 26በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ ያለ​ውን የአ​ደ​ባ​ባ​ዩን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥#ዕብ. “አው​ታ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም” የሚል ይጨ​ም​ራል። ለማ​ገ​ል​ገ​ልም የሚ​ሠ​ሩ​በ​ትን ዕቃ ሁሉ ይሸ​ከሙ፤ በዚ​ህም ያገ​ል​ግሉ። 27የጌ​ድ​ሶን ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ፥ በተ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ፥ በሥ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ትእ​ዛዝ ይሁን፤ በስ​ማ​ቸ​ውና በተ​ራ​ቸ​ውም ትቈ​ጥ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ። 28የጌ​ድ​ሶን ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ ይህ ነው፤ ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ይሆ​ናሉ።
የሜ​ራሪ ልጆች ተግ​ባር
29“የሜ​ራ​ሪ​ንም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች ቍጠ​ራ​ቸው። 30የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት#ዕብ. “ሠላሳ” ይላል። ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠ​ራ​ቸው። 31በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ ባለው አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ሁሉ፥ የድ​ን​ኳኑ ሳን​ቆች፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹም፥ ተራ​ዳ​ዎ​ቹም፥ እግ​ሮ​ቹም፥ መሸ​ፈ​ኛ​ዎ​ቹም፥ መቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም፥ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥ 32በዙ​ሪ​ያ​ውም የሚ​ቆ​ሙት የአ​ደ​ባ​ባዩ ምሰ​ሶ​ዎች፥ እግ​ሮ​ቹም፥ የአ​ደ​ባ​ባዩ ደጃፍ መጋ​ረጃ ምሰ​ሶ​ዎች፥ እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም፥ ካስ​ማ​ዎ​ቹም፥ አው​ታ​ሮ​ቹም፥ ዕቃ​ዎ​ቹና ማገ​ል​ገ​ያ​ዎቹ ሸክ​ማ​ቸው ነው፤ የሚ​ጠ​ብ​ቁ​ት​ንም የሸ​ክ​ማ​ቸ​ውን ዕቃ ሁሉ በየ​ስ​ማ​ቸው ቍጠሩ። 33በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ ባለው ሥራ​ቸው ሁሉ የሜ​ራሪ ልጆች ወገ​ኖች አገ​ል​ግ​ሎት ይህ ነው፤ እነ​ር​ሱም ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ይሆ​ናሉ።”
የሌ​ዋ​ው​ያን ቈጠራ
34ሙሴና አሮ​ንም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አለ​ቆች የቀ​ዓ​ትን ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች ቈጠ​ሩ​አ​ቸው። 35በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ወደ አገ​ል​ግ​ሎት የገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉ​ትን ቈጠ​ሩ​አ​ቸው፤ 36በየ​ወ​ገ​ና​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሁለት ሺህ ሰባት መቶ አምሳ ነበሩ። 37እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ፥ ሙሴና አሮን እንደ ቈጠ​ሩ​አ​ቸው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ የሚ​ገ​ቡት ሁሉ፥ የቀ​ዓት ልጆች ቍጥር ይህ ነው።
38የጌ​ድ​ሶ​ን​ንም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች፥ 39በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የገ​ቡት ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉ​ትን ቈጠ​ሩ​አ​ቸው። 40ቍጥ​ራ​ቸ​ውም በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች ሁለት ሺህ ስድ​ስት መቶ አምሳ ነበር። 41እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ፥ ሙሴና አሮን የቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ያገ​ለ​ገ​ሉት ሁሉ የጌ​ድ​ሶን ልጆች ቍጥር ይህ ነው።
42የሜ​ራ​ሪ​ንም ልጆች ወገ​ኖች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች፥ 43በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ወደ አገ​ል​ግ​ሎት የገ​ቡት ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉ​ትን ቈጠ​ሯ​ቸው። 44ቍጥ​ራ​ቸ​ውም በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች ሦስት ሺህ ሁለት መቶ ነበረ። 45እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ ሙሴና አሮን የቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው የሜ​ራሪ ልጆች ወገ​ኖች ቍጥር ይህ ነው።
46በየ​ወ​ገ​ና​ቸ​ውና በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ከሌ​ዋ​ው​ያን የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሁሉ፥ ሙሴና አሮን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አለ​ቆች የቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው፥ 47በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ሥራ​ውን ለመ​ሥ​ራ​ትና ዕቃ​ውን ለመ​ሸ​ከም የገ​ቡት ሁሉ፥ ከሃያ አም​ስት ዓመት#ዕብ. “ሠላሳ” ይላል። ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ያሉት፥ 48ከእ​ነ​ርሱ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ስም​ንት ሺህ አም​ስት መቶ ሰማ​ንያ#ግእዙ “ስም​ንት ሽህ ሰባት መቶ” ይላል። ነበሩ። 49እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውና በየ​ሸ​ክ​ማ​ቸው በሙሴ እጅ ተቈ​ጠሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ እን​ዲሁ በእ​ርሱ ተቈ​ጠሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ