የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 28

28
የዘ​ወ​ትር መሥ​ዋ​ዕት
(ዘፀ. 29፥38-46)
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 2“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ ቍር​ባ​ኔን፥ መባ​ዬ​ንና የበጎ መዓዛ መሥ​ዋ​ዕ​ቴን በበ​ዓ​ላት ቀኖች ታቀ​ር​ቡ​ልኝ ዘንድ ጠብቁ። 3እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ በእ​ሳት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ታ​ቀ​ር​ቡት ቍር​ባን ይህ ነው፤ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሁለት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ዕለት ዕለት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። 4አን​ዱን ጠቦት በማ​ለዳ፥ ሌላ​ው​ንም ጠቦት በማታ አቅ​ርቡ፤ 5ለእ​ህ​ልም ቍር​ባን የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ በሆነ፥ ተወ​ቅጦ በተ​ጠ​ለለ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ እጅ መል​ካም ዱቄት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። 6በእ​ሳት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የቀ​ረበ፥ በሲና ተራራ የተ​ሠራ ለዘ​ወ​ትር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው። 7የመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ለአ​ንድ ጠቦት የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተ​ኛው እጅ ነው፤ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ጠጥ ቍር​ባን መጠጥ ታፈ​ስ​ሳ​ላ​ችሁ። 8ሌላ​ው​ንም ጠቦት በማታ ጊዜ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና የመ​ጠ​ጡን ቍር​ባን በማ​ለዳ እን​ዳ​ቀ​ረ​ባ​ችሁ በእ​ሳት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ታቀ​ር​ቡ​ታ​ላ​ችሁ።
የሰ​ን​በት መሥ​ዋ​ዕት
9“በሰ​ን​በ​ትም ቀን ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሁለት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ ለእ​ህ​ልም ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። 10በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ሌላ፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ፥ በየ​ሰ​ን​በቱ ሁሉ የም​ታ​ቀ​ር​ቡት የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ይህ ነው።
በመ​ባቻ የሚ​ቀ​ርብ መሥ​ዋ​ዕት
11“በወ​ሩም መባቻ ለእ​ግ​ዚ​አ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ከላ​ሞች ሁለት፥ አንድ አውራ በግ፥ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ 12ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወይ​ፈን ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ መል​ካም ዱቄት፥ ለአ​ው​ራው በግ ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ፥ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት፥ 13ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ጠቦት ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ፥ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። 14የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም ለአ​ንድ ወይ​ፈን የኢን ግማሽ፥ ለአ​ው​ራው በግም የኢን ሲሦ፥ ለአ​ን​ዱም ጠቦት የኢን አራ​ተኛ እጅ የወ​ይን ጠጅ ይሆ​ናል፤ ይህ ለዓ​መቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው። 15ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ​ኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከመ​ጠጡ ቍር​ባን ሌላ ይቀ​ር​ባል።
በፋ​ሲ​ካና በበ​ዓለ ናዕት የሚ​ቀ​ርብ መሥ​ዋ​ዕት
(ዘሌ. 23፥5-14)
16“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ነው። 17በዚ​ህም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በዓል ይሆ​ናል፤ ሰባት ቀን ቂጣ እን​ጀራ ትበ​ላ​ላ​ችሁ። 18የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የተ​ቀ​ደሰ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ በእ​ር​ሱም የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት። 19በእ​ሳ​ትም የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ከላ​ሞች ሁለት በሬ​ዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ። 20የእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንም በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት፥ ለአ​ንድ ወይ​ፈን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአ​ው​ራ​ውም በግ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ፥ 21ለሰ​ባ​ቱም ጠቦ​ቶች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጠቦት ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። 22ማስ​ተ​ስ​ረያ የሚ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁን ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። 23ማልዶ ከሚ​ቀ​ር​በው በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሌላ እነ​ዚ​ህን ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። 24ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ቍር​ባ​ንና መሥ​ዋ​ዕት ሰባት ቀን በየ​ዕ​ለቱ እን​ዲሁ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከመ​ጠጡ ቍር​ባን ሌላ ይቀ​ር​ባል። 25ሰባ​ተ​ኛ​ውም ቀን የተ​ቀ​ደሰ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት።
በበ​ዓለ ሠዊት የሚ​ቀ​ርብ መሥ​ዋ​ዕት
(ዘሌ. 23፥15-22)
26“በበ​ዓለ ሠዊት ቀን በሰ​ን​በ​ታት በዓ​ላ​ችሁ አዲ​ሱን የእ​ህል ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባቀ​ረ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ የተ​ቀ​ደሰ ቀን ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​በት። 27ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ከላ​ሞች ሁለት በሬ​ዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ 28ለእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸው በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት፥ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ወይ​ፈን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአ​ን​ዱም አውራ በግ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ፥ 29ለሰ​ባ​ቱም ጠቦ​ቶች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጠቦት ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። 30ማስ​ተ​ስ​ረያ የሚ​ሆ​ን​ላ​ች​ሁን ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። 31በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን ሌላ እነ​ር​ሱ​ንና የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ቸው ይሁኑ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ