የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 27:15-23

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 27:15-23 አማ2000

ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ “የሥ​ጋና የነ​ፍስ ሁሉ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሕዝብ ላይ የሚ​ሆ​ነ​ውን ሰው ይሹም፤ በፊ​ታ​ቸው የሚ​ወ​ጣ​ው​ንና የሚ​ገ​ባ​ውን፥ የሚ​ያ​ስ​ወ​ጣ​ቸ​ው​ንና፥ የሚ​ያ​ስ​ገ​ባ​ቸ​ው​ንም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር እረኛ እን​ደ​ሌ​ለው መንጋ እን​ዳ​ይ​ሆን።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ያለ​በ​ትን ሰው የነ​ዌን ልጅ ኢያ​ሱን ወስ​ደህ እጅ​ህን በላዩ ጫን​በት፤ በካ​ህ​ኑም በአ​ል​ዓ​ዛር ፊት አቁ​መው፤ በማ​ኅ​በ​ሩም ፊት እዘ​ዘው፤ ስለ እር​ሱም በፊ​ታ​ቸው እዘዝ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እን​ዲ​ታ​ዘ​ዙት ከክ​ብ​ርህ ስጠው። በካ​ህ​ኑም በአ​ል​ዓ​ዛር ፊት ይቁም፤ እር​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ፍርድ ይጠ​ይ​ቅ​ለት፤ እርሱ ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፤ በቃ​ሉም ይግቡ።” ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ፤ ኢያ​ሱ​ንም ወስዶ በካ​ህኑ በአ​ል​ዓ​ዛ​ርና በማ​ኅ​በሩ ሁሉ ፊት አቆ​መው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እንደ አዘ​ዘው፥ እጁን በላዩ ጫነ​በ​ትና፥ ሾመው፤ አዘ​ዘ​ውም።