የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 25

25
ሞዐ​ባ​ው​ያን እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንን በፌ​ጎር እንደ አሳቱ
1እስ​ራ​ኤ​ልም በሰ​ጢን አደሩ፤ ሕዝ​ቡም ከሞ​ዓብ ልጆች ጋር አመ​ነ​ዘሩ፤ ረከ​ሱም። 2ሕዝ​ቡ​ንም ወደ አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው መሥ​ዋ​ዕት ጠሩ፤ ሕዝ​ቡም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን በሉ፤ ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውም ሰገዱ። 3እስ​ራ​ኤ​ልም ለብ​ዔል ፌጎር ራሳ​ቸ​ውን ለዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ። 4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ስላ​ፈ​ረሱ የሕ​ዝ​ቡን አለ​ቆች ሁሉ ወስ​ደህ በፀ​ሐይ ፊት ቅጣ​ቸው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ ከእ​ስ​ራ​ኤል ይር​ቃል።” 5ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሕዝ​ቦች፥ “እና​ንተ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ብዔል ፌጎ​ርን የተ​ከ​ተ​ሉ​ትን ሰዎ​ቻ​ች​ሁን ግደሉ” አላ​ቸው።
6እነ​ሆም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አንዱ መጥቶ በሙ​ሴና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ፊት ወን​ድ​ሙን ወደ ምድ​ያ​ማ​ዊት ሴት ወሰ​ደው፤#ዕብ. “ምድ​ያ​ማ​ዊ​ቱን ሴት ወደ ወን​ድ​ሞቹ አመ​ጣት” ይላል። እነ​ር​ሱም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዳጃፍ ያለ​ቅሱ ነበር። 7የካ​ህ​ኑም የአ​ሮን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ ባየው ጊዜ ከማ​ኅ​በሩ መካ​ከል ተነ​ሥቶ በእጁ ጦር አነሣ። 8ያንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰው ተከ​ትሎ ወደ ድን​ኳኑ ገባ። ሁለ​ቱ​ንም እስ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ውን ሰውና ምድ​ያ​ማ​ዊ​ቱን ሴት ሆዳ​ቸ​ውን ወጋ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መቅ​ሠ​ፍቱ ተወ​ገደ። 9በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ቱም የሞ​ቱት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ።
10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 11“የካ​ህኑ የአ​ሮን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ በቅ​ን​ዓቴ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቀን​ቶ​አ​ልና ቍጣ​ዬን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መለሰ፤ እኔም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በቅ​ን​ዓቴ አላ​ጠ​ፋ​ሁም። 12ስለ​ዚህ አልሁ፦ እነሆ፥ የሰ​ላ​ሜን ቃል ኪዳን እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ። 13ለአ​ም​ላኩ ቀን​ቶ​አ​ልና፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አስ​ተ​ስ​ር​ዮ​አ​ልና፥ ለእ​ርሱ ከእ​ር​ሱም በኋላ ለዘሩ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የክ​ህ​ነት ቃል ኪዳን ይሆ​ን​ለ​ታል።”
14ከም​ድ​ያ​ማ​ዊ​ቱም ጋር የተ​ገ​ደ​ለው የእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ሰው ስም ዘን​በሪ ነበረ፤ የአ​ባቱ ቤት አለቃ የስ​ም​ዖ​ና​ው​ያን የሆነ የሰሉ ልጅ ነበረ። 15የተ​ገ​ደ​ለ​ች​ውም ምድ​ያ​ማ​ዊት ስምዋ ከስቢ ነበረ፤ እር​ስ​ዋም የሱር ልጅ ነበ​ረች፤ እር​ሱም የም​ድ​ያም አባ​ቶች ወገን የሚ​ሆን የሳ​ሞት ወገን አለቃ ነበረ።
16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ 17ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንን አስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው፤ ግደ​ሉ​አ​ቸ​ውም። 18ስለ ምድ​ያም አለቃ ልጅ ስለ እኅ​ታ​ቸው ስለ ከስቢ በፌ​ጎር ምክ​ን​ያት በሸ​ነ​ገ​ሉ​አ​ችሁ ሽን​ገላ አስ​ጨ​ን​ቀ​ዋ​ች​ኋ​ልና።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ