መጽ​ሐፈ ነህ​ምያ 8:1-8

መጽ​ሐፈ ነህ​ምያ 8:1-8 አማ2000

ሰባ​ተ​ኛ​ውም ወር በደ​ረሰ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ነበሩ። ሕዝ​ቡም ሁሉ በው​ኃው በር ፊት ወዳ​ለው አደ​ባ​ባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል ያዘ​ዘ​ውን የሙ​ሴን ሕግ መጽ​ሐፍ ያመጣ ዘንድ ጸሓ​ፊ​ውን ዕዝ​ራን ነገ​ሩት። ካህ​ኑም ዕዝራ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ሕጉን በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች ጉባኤ፥ አስ​ተ​ው​ለ​ውም በሚ​ሰ​ሙት ሁሉ ፊት አመ​ጣው። በው​ኃ​ውም በር ፊት ባለው አደ​ባ​ባይ ላይ ቆሞ፥ በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች በሚ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉ​ትም ፊት፥ ከማ​ለዳ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ አነ​በ​በው፤ የሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ጆሮ የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ ለመ​ስ​ማት ያደ​ምጥ ነበር። ጸሓ​ፊ​ውም ዕዝራ ስለ​ዚህ ነገር በተ​ሠራ በዕ​ን​ጨት መረ​ባ​ርብ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአ​ጠ​ገቡ መቲ​ትያ፥ ሰምያ፥ ሐና​ንያ፤ ኦርያ፥ ሕል​ቅያ፥ መዕ​ሢያ በቀኙ በኩል፥ ፈድያ፥ ሚሳ​ኤል፥ ሚል​ክያ፥ ሐሱም፥ ሐስ​በ​ዳና፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ሜሱ​ላም በግ​ራው በኩል ቆመው ነበር። ዕዝ​ራም የሕ​ዝቡ ሁሉ የበ​ላይ ነበ​ረና በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት መጽ​ሐ​ፉን ገለጠ፤ በገ​ለ​ጠ​ውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። ዕዝ​ራም ታላ​ቁን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገነ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እጃ​ቸ​ውን እየ​ዘ​ረጉ፥ “አሜን፥ አሜን” ብለው መለሱ። ራሳ​ቸ​ው​ንም አዘ​ነ​በሉ፤ በግ​ን​ባ​ራ​ቸ​ውም ወደ ምድር ተደ​ፍ​ተው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገዱ። ደግሞ ኢያ​ሱና ባኒ፥ ሰራ​ብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሳባ​ታይ፥ ሆዲያ፥ መዕ​ሤያ፥ ቆሊጣ፥ ዓዛ​ርያ፥ ኢዮ​ዛ​ባድ፥ ሐናን፥ ፌል​ዕያ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ሕጉን ለሕ​ዝቡ ያስ​ተ​ምሩ ነበር፤ ሕዝ​ቡም በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው ቆመው ነበር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕግ መጽ​ሐፍ አነ​በቡ፤ ዕዝ​ራም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማወቅ ያስ​ተ​ም​ርና ያስ​ታ​ውቅ ነበር፤ ሕዝ​ቡም የሚ​ነ​በ​በ​ውን ያስ​ተ​ውሉ ነበር።