የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነህ​ምያ 5

5
1በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም በአ​ይ​ሁድ ላይ ትልቅ የሕ​ዝ​ቡና የሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸው ጩኸት ሆነ። 2“ከወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችን ጋር ብዙ​ዎች ነን፤ በል​ተ​ንም በሕ​ይ​ወት እን​ድ​ን​ኖር እህ​ልን እን​ሸ​ምት” የሚሉ ነበሩ። 3“ከራብ የተ​ነ​ሣም#“ከራብ የተ​ነሣ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። እህ​ልን እን​ሸ​ምት ዘንድ እር​ሻ​ች​ን​ንና ወይ​ና​ች​ንን፥ ቤታ​ች​ን​ንም አስ​ይ​ዘ​ናል” የሚሉ ነበሩ። 4ሌሎ​ቹም “ለን​ጉሡ ግብር እር​ሻ​ች​ን​ንና ወይ​ና​ች​ንን አስ​ይ​ዘን ገን​ዘብ ተበ​ድ​ረ​ናል፤ 5አሁ​ንም ሥጋ​ችን እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሥጋ፥ ልጆ​ቻ​ች​ንም እንደ ልጆ​ቻ​ቸው ናቸው፤ እነ​ሆም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችን ባሪ​ያ​ዎች ይሆኑ ዘንድ ሰጥ​ተ​ናል፤ ከሴ​ቶ​ችም ልጆ​ቻ​ችን ባሪ​ያ​ዎች ሆነው የሚ​ኖሩ አሉ፤ ታላ​ላ​ቆ​ችም እር​ሻ​ች​ን​ንና ወይ​ና​ች​ንን ይዘ​ዋ​ልና ልና​ድ​ና​ቸው አን​ች​ልም” የሚሉ ነበሩ።
6እኔም ጩኸ​ታ​ቸ​ው​ንና ይህን ቃል በሰ​ማሁ ጊዜ እጅግ ዐዘ​ንሁ።#ዕብ. “ተቈ​ጣሁ” ይላል። 7በል​ቤም አሰ​ብሁ፤ ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹ​ንም፥ “ሁላ​ችሁ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ወለድ ትወ​ስ​ዳ​ላ​ችሁ” ብዬ ተጣ​ላ​ኋ​ቸው፤ ትል​ቅም ጉባኤ ሰበ​ሰ​ብ​ሁ​ባ​ቸው። 8እኔም፥ “ለአ​ሕ​ዛብ የተ​ሸ​ጡ​ትን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንን አይ​ሁ​ድን በፈ​ቃ​ዳ​ችን ተቤ​ዠን፤ እና​ን​ተስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ትሸ​ጣ​ላ​ች​ሁን? እነ​ር​ሱስ ለእኛ የተ​ሸጡ ይሆ​ና​ሉን?” አል​ኋ​ቸው። እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ መል​ስም አላ​ገ​ኙም። 9ደግ​ሞም አልሁ፥ “የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ችን አሕ​ዛብ እን​ዳ​ይ​ሰ​ድ​ቡን አም​ላ​ካ​ች​ንን በመ​ፍ​ራት ትሄዱ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ች​ሁ​ምን? 10እኔ ደግሞ፥ ወን​ድ​ሞ​ችም፥ ብላ​ቴ​ኖ​ችም ገን​ዘ​ብና እህል ለእ​ነ​ርሱ አበ​ድ​ረ​ናል፤ እባ​ካ​ችሁ፥ ይህን ወለድ እን​ተ​ው​ላ​ቸው። 11እር​ሻ​ቸ​ውን፥ የወ​ይ​ና​ቸ​ው​ንና የወ​ይ​ራ​ቸ​ውን ቦታ፥ ቤታ​ቸ​ው​ንም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም የወ​ሰ​ዳ​ች​ሁ​ትን ገን​ዘ​ቡ​ንና እህ​ሉን፥ ወይን ጠጁ​ንና ዘይ​ቱን#ዕብ. “ከመቶ እጅ አንድ እጅ” ይላል። እባ​ካ​ችሁ ዛሬ መል​ሱ​ላ​ቸው።” 12እነ​ር​ሱም፥ “እን​መ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ምንም አን​ሻም፤ እን​ደ​ተ​ና​ገ​ርህ እን​ዲሁ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉ። ካህ​ና​ቱ​ንም ጠርቼ እን​ደ​ዚህ ነገር ያደ​ርጉ ዘንድ አማ​ል​ኋ​ቸው። 13ደግ​ሞም ልብ​ሴን አራ​ገ​ፍ​ሁና፥ “ይህን ነገር የማ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ሰው ከቤ​ቱና ከሥ​ራው እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያራ​ግ​ፈው፤ እን​ዲሁ የተ​ራ​ገ​ፈና ባዶ ይሁን” አልሁ። ጉባ​ኤ​ውም ሁሉ፥ “አሜን” አሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገኑ፤ ሕዝ​ቡም እን​ደ​ዚህ ነገር አደ​ረጉ።
14ንጉ​ሡም በይ​ሁዳ ምድር ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ካዘ​ዘኝ ጊዜ ጀምሮ ከን​ጉሡ ከአ​ር​ተ​ሰ​ስታ ከሃ​ያ​ኛው ዓመት እስከ ሠላሳ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት ድረስ ዐሥራ ሁለት ዓመት ያህል እኔና ወን​ድ​ሞች ለአ​ለቃ የሚ​ገ​ባ​ውን ቀለብ አል​በ​ላ​ንም። 15ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው የነ​በ​ሩት አለ​ቆች ግን በሕ​ዝቡ ላይ አክ​ብ​ደው ነበር፤ ስለ እን​ጀ​ራ​ውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወ​ስዱ ነበር፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሕ​ዝቡ ላይ ይሰ​ለ​ጥኑ ነበር። እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ፈራሁ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ግ​ሁም። 16ደግ​ሞም የቅ​ጥ​ሩን ሥራ ሠራሁ፤ እር​ሻም አል​ገ​ዛ​ሁም፤ ብላ​ቴ​ኖ​ችም ሁሉ ወደ​ዚ​ያው ወደ ሥራው ተሰ​በ​ሰቡ። 17ደግ​ሞም በዙ​ሪ​ያ​ችን ካሉት አሕ​ዛብ ወደ እኛ ከመ​ጡት ሌላ ከአ​ይ​ሁ​ድና ከሹ​ሞቹ#“ከሹ​ሞቹ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። መቶ አምሳ ሰዎች በገ​በ​ታዬ ነበሩ። 18ለአ​ንድ ቀን አንድ በሬና ስድ​ስት የሰቡ በጎች፥ አንድ ፍየ​ልም፥ በዐ​ሥር በዐ​ሥር ቀንም ብዙ ልዩ ልዩ ዓይ​ነት ወይን ጠጅ ይዘ​ጋ​ጅ​ልኝ ነበር፤ ነገር ግን አገ​ዛዝ በሕ​ዝቡ ላይ ከብዶ ነበ​ርና ለአ​ለቃ የሚ​ገ​ባ​ውን ቀለብ አል​ሻም ነበር። 19አም​ላኬ ሆይ፥ ለዚህ ሕዝብ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ሁሉ ለበ​ጎ​ነት አስ​ብ​ልኝ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ