የማ​ር​ቆስ ወን​ጌል 14:33-36

የማ​ር​ቆስ ወን​ጌል 14:33-36 አማ2000

ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ሊደነግጥም ሊተክዝም ጀመረና “ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቈዩ፤ ትጉም፤” አላቸው። ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በምድርም ወድቆ፥ ይቻልስ ቢሆን ሰዓቲቱ ከእርሱ እንድታልፍ ጸለየና “አባ አባት ሆይ! ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን፤” አለ።