መዝሙርም ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ወጡ። ኢየሱስም “በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ ‘እረኛዉን እመታለሁ፤ በጎችም ይበተናሉ፤’ የሚል ተጽፎአልና። ነገር ግን ከተነሣሁ በኋላ ወደ ገሊላ እቀድማችኋለሁ፤” አላቸው። ጴጥሮስም “ሁሉም ቢሰናከሉ እኔ ግን ከቶ አልሰናከልም፤” አለው። ኢየሱስም “እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ በዚች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” አለው። እርሱም ቃሉን አበርትቶ “ከአንተ ጋር የምሞት እንኳ ቢሆን ከቶ አልክድህም፤” አለ። ሁሉም ደግሞ እንደዚሁ አሉ። ጌቴሴማኒ ወደምትባልም ስፍራ መጡ፤ ደቀ መዛሙርቱንም “ስጸልይ ሳለሁ፥ በዚህ ተቀመጡ፤” አላቸው። ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ሊደነግጥም ሊተክዝም ጀመረና “ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቈዩ፤ ትጉም፤” አላቸው። ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በምድርም ወድቆ፥ ይቻልስ ቢሆን ሰዓቲቱ ከእርሱ እንድታልፍ ጸለየና “አባ አባት ሆይ! ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን፤” አለ። መጣም፤ ተኝተውም አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም “ስምዖን ሆይ! ተኝተሃልን? አንዲት ሰዓት ስንኳ ልትተጋ አልቻልህምን? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ፤ ጸልዩም፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው፤” አለው። ደግሞም ሄዶ ያንኑ ቃል ጸለየ። ደግሞም መጥቶ ዐይኖቻቸው በእንቅልፍ ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸው፤ የሚመልሱለትንም አላወቁም። ሦስተኛም መጥቶ “እንግዲህስ ተኙ፤ ዕረፉም፤ ይበቃል፤ ሰዓቲቱ ደረሰች፤ እነሆ፥ የሰው ልጅ በኀጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል። ተነሡ፤ እንሂድ፤ እነሆ፥ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቦአል፤” አላቸው። ወዲያውም ገና ሲናገር ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፤ ከእርሱም ጋር ብዙ ሰዎች ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከጻፎች ከሽማግሌዎችም ዘንድ መጡ። አሳልፎ የሚሰጠውም “የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት፤ ተጠንቅቃችሁም ውሰዱት፤” ብሎ ምልክት ሰጥቶአቸው ነበር። መጥቶም ወዲያው ወደ እርሱ ቀረበና “መምህር ሆይ! መምህር ሆይ!” ብሎ ሳመው፤ እነርሱም እጃቸውን በእርሱ ላይ ጭነው ያዙት። በአጠገብ ከቆሙት ግን አንዱ ሰይፉን መዞ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መታ፤ ጆሮውንም ቈረጠ። ኢየሱስም መልሶ “ወንበዴ እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ መጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስኖር አልያዛችሁኝም፤ ነገር ግን መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ይህ ሆነ፤” አላቸው። ሁሉም ትተውት ሸሹ።
የማርቆስ ወንጌል 14 ያንብቡ
ያዳምጡ የማርቆስ ወንጌል 14
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የማርቆስ ወንጌል 14:26-50
16 ቀናት
የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት እና ትንሣኤ በአራቱ ወንጌላት ውስጥ ተገልፆል። ይህ የፋሲካ በዓል የሚነግረን ፣ እንዴት ኢየሱስ ክርስቶስ መራራ ፅዋን፣ መከራን እና ስቃይን በመስቀል ላይ ተቀብሎ ከሞት በመነሳቱ በትንሳኤው ለአለም ሁሉ የምስራች ዜናን አበሰረ ። ይህ አጭር ቪዲዮ ፣ የእያንዳንዱ ቀን ታሪክ በምሳሌ ይገልፃል።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች