የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 8:22-25

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 8:22-25 አማ2000

ከዕ​ለ​ታት በአ​ን​ዲት ቀንም እን​ዲህ ሆነ፤ እርሱ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ ታንኳ ወጣና፥ “ኑ ወደ ባሕሩ ማዶ እን​ሻ​ገር” አላ​ቸው እነ​ር​ሱም ሄዱ። ሲሄ​ዱም አን​ቀ​ላፋ፤ በባ​ሕ​ሩም ላይ ዐውሎ ነፋስ መጣ፤ ውኃ​ዉም ታን​ኳ​ቸ​ውን ሞላው፤ እነ​ር​ሱም ተጨ​ነቁ። ቀር​በ​ውም፥ “መም​ህር ሆይ፥ መም​ህር ሆይ፥ ልን​ጠፋ ነው” ብለው ቀሰ​ቀ​ሱት፤ ተነ​ሥ​ቶም ነፋ​ሱ​ንና የው​ኃ​ዉን ማዕ​በል ገሠ​ጻ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ ታላቅ ፀጥ​ታም ሆነ። እር​ሱም “እም​ነ​ታ​ችሁ ወዴት አለ?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ፈር​ተው ተደ​ነቁ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ውኃም ነፋ​ስም የሚ​ታ​ዘ​ዙ​ለት ይህ ማነው?” አሉ።