የሉ​ቃስ ወን​ጌል 4:38-41

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 4:38-41 አማ2000

ከም​ኵ​ራ​ቡም ወጥቶ ወደ ስም​ዖን ቤት ገባ፤ የስ​ም​ዖን አማ​ትም በብ​ርቱ ንዳድ ታማ ነበ​ርና ስለ እር​ስዋ ነገ​ሩት። በአ​ጠ​ገ​ብ​ዋም ቁሞ ንዳ​ድ​ዋን ገሠ​ጸ​ውና ተዋት፤ ወዲ​ያ​ውም ተነ​ሥታ አገ​ለ​ገ​ለ​ቻ​ቸው። ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ልዩ ልዩ ደዌ ያለ​ባ​ቸ​ውን ድው​ያን ሁሉ አመ​ጡ​ለት፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ላይ እጁን ጭኖ ፈወ​ሳ​ቸው። ብዙ አጋ​ን​ን​ትም፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ክር​ስ​ቶስ ነህ” እያ​ሉና እየ​ጮሁ ይወጡ ነበር፤ እር​ሱም ይገ​ሥ​ጻ​ቸው ነበር፤ ክር​ስ​ቶ​ስም እንደ ሆነ ያውቁ ነበ​ርና እን​ዲ​ና​ገሩ አይ​ፈ​ቅ​ድ​ላ​ቸ​ውም ነበር።