የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 22:58-62

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 22:58-62 አማ2000

ከጥ​ቂት ጊዜም በኋላ ሌላ ሰው አየ​ውና፥ “አን​ተም ከእ​ነ​ርሱ ወገን ነህ” አለው፤ ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አንተ ሰው! እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም” አለው። አን​ዲት ሰዓት ያህ​ልም ቈይቶ አንድ ሌላ ሰው፥ “ይህም በእ​ው​ነት ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ሰው​የ​ውም የገ​ሊላ ሰው ነው” ብሎ አስ​ጨ​ነ​ቀው። ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አንተ ሰው! የም​ት​ለ​ውን አላ​ው​ቅም” አለው፤ እር​ሱም ይህን ሲና​ገር ያን​ጊዜ ዶሮ ጮኸ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዘወር ብሎ ጴጥ​ሮ​ስን አየው፤ ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ዛሬ ዶሮ ሳይ​ጮኽ ሦስት ጊዜ ትክ​ደ​ኛ​ለህ” ያለ​ውን የጌ​ታ​ች​ንን ቃል ዐሰበ። ጴጥ​ሮ​ስም ወደ ውጭ ወጥቶ መራራ ልቅ​ሶን አለ​ቀሰ።