የሉ​ቃስ ወን​ጌል 22:29-46

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 22:29-46 አማ2000

አባቴ ለእኔ እንደ ሰጠኝ፥ እኔም ለእ​ና​ንተ መን​ግ​ሥ​ትን አዘ​ጋ​ጅ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በመ​ን​ግ​ሥቴ በማ​ዕዴ ትበ​ሉና ትጠጡ ዘንድ፥ በወ​ን​በ​ሮ​ችም ተቀ​ም​ጣ​ችሁ በዐ​ሥራ ሁለቱ ነገደ እስ​ራ​ኤል ትፈ​ርዱ ዘንድ።” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ስም​ዖን፥ ስም​ዖን ሆይ፥ ሰይ​ጣን እንደ አጃ ሊያ​በ​ጥ​ራ​ችሁ አሁን ልመ​ናን ለመነ። እኔ ግን ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ደ​ክም ስለ እና​ንተ ጸለ​ይሁ፤ አን​ተም ተመ​ል​ሰህ ወን​ድ​ሞ​ች​ህን አጽ​ና​ቸው።” እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ እኔ ለመ​ታ​ሰ​ርም ቢሆን፥ ለሞ​ትም ቢሆን እንኳ ከአ​ንተ ጋራ ለመ​ሄድ የተ​ዘ​ጋ​ጀሁ ነኝ” አለው። እርሱ ግን፥ “ጴጥ​ሮስ ሆይ፥ እል​ሃ​ለሁ፥ ዛሬ ዶሮ ሳይ​ጮኽ እን​ደ​ማ​ታ​ው​ቀኝ ሦስት ጊዜ ትክ​ደ​ኛ​ለህ” አለው። ደግ​ሞም፥ “ያለ ስልቻ፥ ያለ ከረ​ጢ​ትና ያለ ጫማ በላ​ክ​ኋ​ችሁ ጊዜ በውኑ የተ​ቸ​ገ​ራ​ች​ሁት ነገር ነበ​ርን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የለም” አሉት። እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አሁን ግን ኮሮጆ ያለው ኮሮ​ጆ​ውን ይያዝ፤ ከረ​ጢ​ትም ያለው እን​ዲሁ ያድ​ርግ፤ ሰይፍ የሌ​ለ​ውም ልብ​ሱን ሸጦ ሰይፍ ይግዛ። እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ተቈ​ጠረ ተብሎ የተ​ጻ​ፈው በእኔ ይደ​ር​ሳል፤ ስለ እኔ የተ​ጻ​ፈ​ውም ሁሉ ይፈ​ጸ​ማል።” እነ​ር​ሱም፥ “አቤቱ፥ እነሆ፥ እዚህ በእኛ ዘንድ ሁለት ሰይ​ፎች አሉ” አሉት፤ እር​ሱም፥ “እን​ግ​ዲ​ያስ ይበ​ቃ​ች​ኋል” አላ​ቸው። ወጥ​ቶም እን​ዳ​ስ​ለ​መ​ደው ይጸ​ልይ ዘንድ ወደ ደብረ ዘይት ሄደ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ተከ​ተ​ሉት። ከዚ​ያም ደርሶ፥ “ወደ መከራ እን​ዳ​ት​ገቡ ጸልዩ” አላ​ቸው። የድ​ን​ጋይ ውር​ወራ ያህ​ልም ከእ​ነ​ርሱ ፈቀቅ ብሎ እየ​ሰ​ገደ ጸለየ። እን​ዲ​ህም አለ፥ “አባት ሆይ፥ ብት​ፈ​ቅ​ድስ ይህን ጽዋ ከእኔ አሳ​ል​ፈው፤ ነገር ግን የአ​ንተ ፈቃድ ይሁን እንጂ የእኔ ፈቃድ አይ​ሁን።” የሚ​ያ​በ​ረ​ታ​ታው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ከሰ​ማይ ታየው። ፈራ፤ መላ​ል​ሶም ጸለየ፤ ላቡም በም​ድር ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ ደም ነጠ​ብ​ጣብ ሆነ። ከሚ​ጸ​ል​ይ​በ​ትም ተነ​ሥቶ ወደ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሄደ፤ ከኀ​ዘ​ንም የተ​ነሣ ተኝ​ተው አገ​ኛ​ቸው። “ስለ ምን ትተ​ኛ​ላ​ችሁ? ወደ ፈተና እን​ዳ​ት​ገቡ ተነ​ሡና ጸልዩ” አላ​ቸው።