አባቴ ለእኔ እንደ ሰጠኝ፥ እኔም ለእናንተ መንግሥትን አዘጋጅላችኋለሁ፤ በመንግሥቴ በማዕዴ ትበሉና ትጠጡ ዘንድ፥ በወንበሮችም ተቀምጣችሁ በዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ትፈርዱ ዘንድ።” ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለ፥ “ስምዖን፥ ስምዖን ሆይ፥ ሰይጣን እንደ አጃ ሊያበጥራችሁ አሁን ልመናን ለመነ። እኔ ግን ሃይማኖታችሁ እንዳይደክም ስለ እናንተ ጸለይሁ፤ አንተም ተመልሰህ ወንድሞችህን አጽናቸው።” እርሱም፥ “አቤቱ፥ እኔ ለመታሰርም ቢሆን፥ ለሞትም ቢሆን እንኳ ከአንተ ጋራ ለመሄድ የተዘጋጀሁ ነኝ” አለው። እርሱ ግን፥ “ጴጥሮስ ሆይ፥ እልሃለሁ፥ ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ እንደማታውቀኝ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” አለው። ደግሞም፥ “ያለ ስልቻ፥ ያለ ከረጢትና ያለ ጫማ በላክኋችሁ ጊዜ በውኑ የተቸገራችሁት ነገር ነበርን?” አላቸው፤ እነርሱም፥ “የለም” አሉት። እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “አሁን ግን ኮሮጆ ያለው ኮሮጆውን ይያዝ፤ ከረጢትም ያለው እንዲሁ ያድርግ፤ ሰይፍ የሌለውም ልብሱን ሸጦ ሰይፍ ይግዛ። እላችኋለሁ፥ ከኃጥኣን ጋር ተቈጠረ ተብሎ የተጻፈው በእኔ ይደርሳል፤ ስለ እኔ የተጻፈውም ሁሉ ይፈጸማል።” እነርሱም፥ “አቤቱ፥ እነሆ፥ እዚህ በእኛ ዘንድ ሁለት ሰይፎች አሉ” አሉት፤ እርሱም፥ “እንግዲያስ ይበቃችኋል” አላቸው። ወጥቶም እንዳስለመደው ይጸልይ ዘንድ ወደ ደብረ ዘይት ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱም ተከተሉት። ከዚያም ደርሶ፥ “ወደ መከራ እንዳትገቡ ጸልዩ” አላቸው። የድንጋይ ውርወራ ያህልም ከእነርሱ ፈቀቅ ብሎ እየሰገደ ጸለየ። እንዲህም አለ፥ “አባት ሆይ፥ ብትፈቅድስ ይህን ጽዋ ከእኔ አሳልፈው፤ ነገር ግን የአንተ ፈቃድ ይሁን እንጂ የእኔ ፈቃድ አይሁን።” የሚያበረታታው የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ታየው። ፈራ፤ መላልሶም ጸለየ፤ ላቡም በምድር ላይ እንደሚወርድ እንደ ደም ነጠብጣብ ሆነ። ከሚጸልይበትም ተነሥቶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሄደ፤ ከኀዘንም የተነሣ ተኝተው አገኛቸው። “ስለ ምን ትተኛላችሁ? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተነሡና ጸልዩ” አላቸው።
የሉቃስ ወንጌል 22 ያንብቡ
ያዳምጡ የሉቃስ ወንጌል 22
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሉቃስ ወንጌል 22:29-46
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች