የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 22:14-20

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 22:14-20 አማ2000

ሰዓ​ቱም በደ​ረሰ ጊዜ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በማ​ዕድ ተቀ​መጠ፤ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​መጡ። እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከመ​ከ​ራዬ አስ​ቀ​ድሞ ይህን ፋሲካ ከእ​ና​ንተ ጋር ልበላ እጅግ ወደ​ድሁ። ነገር ግን፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ እን​ግ​ዲህ ከእ​ርሱ እን​ደ​ማ​ል​በላ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው። ጽዋ​ው​ንም ተቀ​ብሎ አመ​ሰ​ገነ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይህን እንኩ ሁላ​ች​ሁም ተካ​ፈ​ሉት። እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እስ​ክ​ት​መጣ ድረስ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ከዚህ የወ​ይን ፍሬ አል​ጠ​ጣም።” ኅብ​ስ​ቱ​ንም አነሣ፤ አመ​ስ​ገነ፤ ፈት​ቶም ሰጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ስለ እና​ንተ ቤዛ ሆኖ የሚ​ሰጥ ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህ​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢ​ያዬ አድ​ር​ጉት፤” እን​ዲ​ሁም ከእ​ራት በኋላ ጽዋ​ዉን አን​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህ ጽዋ ስለ እና​ንተ በሚ​ፈ​ስ​ሰው ደሜ የሚ​ሆን አዲስ ኪዳን ነው።