በሄዱም ጊዜ እንዳላቸው አገኙ፤ የፋሲካውንም በግ አዘጋጁ። ሰዓቱም በደረሰ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ በማዕድ ተቀመጠ፤ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱም ከእርሱ ጋር ተቀመጡ። እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “ከመከራዬ አስቀድሞ ይህን ፋሲካ ከእናንተ ጋር ልበላ እጅግ ወደድሁ። ነገር ግን፤ በእግዚአብሔር መንግሥት እስኪፈጸም ድረስ እንግዲህ ከእርሱ እንደማልበላ እነግራችኋለሁ” አላቸው። ጽዋውንም ተቀብሎ አመሰገነ፤ እንዲህም አለ፥ “ይህን እንኩ ሁላችሁም ተካፈሉት። እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት እስክትመጣ ድረስ፤ እንግዲህ ወዲህ ከዚህ የወይን ፍሬ አልጠጣም።” ኅብስቱንም አነሣ፤ አመስገነ፤ ፈትቶም ሰጣቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ስለ እናንተ ቤዛ ሆኖ የሚሰጥ ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህንም ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋዉን አንሥቶ እንዲህ አላቸው፥ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈስሰው ደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው። “ነገር ግን አሳልፎ የሚሰጠኝ ሰው እጅ እነሆ፥ በማዕድ ከእኔ ጋር ነው። የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ በእጁ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት።” ደቀ መዛሙርቱም ከእነርሱ ይህን የሚያደርግ ማን እንደ ሆነ እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ። ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ማን እንደሚበልጥ እርስ በርሳቸው ተከራከሩ። እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “አሕዛብን ንጉሦቻቸው ይገዙአቸዋል፤ በላያቸውም ሥልጣን ያላቸው ቸርነት አድራጊዎች ይባላሉ። ለእናንተ ግን እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ከእናንተ ታላቁ እንደ ታናሽ ይሁናችሁ፤ አለቃውም እንደ አገልጋይ ይሁን። የሚበልጥ ማንኛው ነው? በማዕድ ላይ የተቀመጠው ነው? ወይስ የሚላላከው? በማዕድ ላይ የተቀመጠው አይደለምን? እነሆ፥ እኔ በመካከላችሁ እንደ አገልጋይ ነኝ። ነገር ግን ስለ እኔ የታገሣችሁ እናንተ በመከራዬ ከእኔ ጋር ናችሁ።
የሉቃስ ወንጌል 22 ያንብቡ
ያዳምጡ የሉቃስ ወንጌል 22
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሉቃስ ወንጌል 22:13-28
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች