የሉ​ቃስ ወን​ጌል 20:20-47

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 20:20-47 አማ2000

ከእ​ነ​ር​ሱም ተለ​ይ​ተው ከሄዱ በኋላ፥ የሚ​ጠ​ባ​በ​ቁ​ትን አዘ​ጋ​ጁ​ለት፤ በአ​ነ​ጋ​ገ​ሩም ያስ​ቱት ዘንድ ወደ መኳ​ን​ን​ትና ወደ መሳ​ፍ​ንት አሳ​ል​ፈው ሊሰ​ጡት ራሳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​መ​ጻ​ድቁ ሰላ​ዮ​ችን ወደ እርሱ ላኩ። እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ብለው ጠየ​ቁት፥ “መም​ህር ሆይ፥ አንተ እው​ነት እን​ደ​ም​ት​ና​ገ​ርና እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር፥ ፊት አይ​ተ​ህም እን​ደ​ማ​ታ​ዳላ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መን​ገድ በቀ​ጥታ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር እና​ው​ቃ​ለን። ለቄ​ሣር ግብር መስ​ጠት ይገ​ባል? ወይስ አይ​ገ​ባም?” ተን​ኰ​ላ​ቸ​ው​ንም ዐውቆ፥ “ለምን ትፈ​ት​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ? ገን​ዘ​ቡን አሳ​ዩኝ” አላ​ቸው። አም​ጥ​ተ​ውም አሳ​ዩት፤ “መልኩ፥ ጽሕ​ፈ​ቱስ የማ​ነው?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የቄ​ሣር ነው” ብለው መለ​ሱ​ለት። እር​ሱም፥ “እን​ኪ​ያስ የቄ​ሣ​ርን ለቄ​ሣር፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጡ” አላ​ቸው። በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት በአ​ነ​ጋ​ገሩ ማሳ​ሳት ተሳ​ና​ቸው፤ መል​ሱ​ንም አድ​ን​ቀው ዝም አሉ። “ሙታን አይ​ነ​ሡም” ከሚሉ ከሰ​ዱ​ቃ​ው​ያ​ንም አን​ዳ​ንድ ሰዎች ወደ እርሱ መጡ። እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ብለው ጠየ​ቁት፥ “መም​ህር ሆይ፥ ሙሴ፦ ‘ወን​ድሙ ልጅ ሳይ​ወ​ልድ ሚስ​ቱን ትቶ የሞ​ተ​በት ሰው ቢኖር ወን​ድሙ ሚስ​ቱን አግ​ብቶ ለወ​ን​ድሙ ዘር ይተካ’ ሲል ጽፎ​ል​ናል። እን​ግ​ዲህ ከእኛ ዘንድ ሰባት ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ነበሩ፤ ታላቁ ሚስት አግ​ብቶ ልጅ ሳይ​ወ​ልድ ሞተ። እን​ደ​ዚ​ሁም ሁለ​ተ​ኛው አገ​ባት፤ እር​ሱም ልጅ ሳይ​ወ​ልድ ሞተ፤ ሦስ​ተ​ኛ​ውም አገ​ባት፤ እን​ዲ​ሁም ሰባቱ ሁሉ አገ​ቡ​አት፤ ልጅ ሳይ​ወ​ል​ዱም ሞቱ። ከሁ​ሉም በኋላ ያቺ ሴት ሞተች። እን​ግ​ዲህ ሙታን በሚ​ነ​ሡ​በት ጊዜ ከእ​ነ​ርሱ ለማ​ን​ኛው ሚስት ትሆ​ና​ለች? ሰባ​ቱም ሁሉ አግ​ብ​ተ​ዋት ነበ​ርና።” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የዚህ ዓለም ልጆች ያገ​ባሉ፥ ይጋ​ባ​ሉም፤ ይወ​ል​ዳሉ፥ ይዋ​ለ​ዳ​ሉም። ያን ዓለ​ምና የሙ​ታ​ንን ትን​ሣኤ ሊወ​ርሱ የሚ​ገ​ባ​ቸው እነ​ዚያ ግን አያ​ገ​ቡም፤ አይ​ጋ​ቡም። እን​ግ​ዲህ ወዲህ ሞት የለ​ባ​ቸ​ውም፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ናቸው እንጂ፤ የት​ን​ሣኤ ልጆ​ችም ስለ​ሆኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ይሆ​ናሉ። ሙታን እን​ደ​ሚ​ነ​ሡስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ‘እኔ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ነኝ’ ብሎ በቍ​ጥ​ቋ​ጦው ዘንድ እንደ አነ​ጋ​ገ​ረው ሙሴ ተና​ግ​ሮ​አል። እን​ኪ​ያስ የሕ​ያ​ዋን አም​ላክ እንጂ የሙ​ታን አም​ላክ አይ​ደ​ለም፤ ሁሉም በእ​ርሱ ዘንድ ሕያ​ዋን ናቸ​ውና።” ከጻ​ፎ​ችም ወገን የሆኑ ሰዎች፥ “መም​ህር ሆይ፥ መል​ካም ብለ​ሃል” ብለው መለሱ። ከዚያ ወዲህ ግን ሊጠ​ይ​ቀው የደ​ፈረ ማንም የለም። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ክር​ስ​ቶ​ስን እን​ዴት የዳ​ዊት ልጅ ይሉ​ታል? እርሱ ራሱ ዳዊት በመ​ዝ​ሙር መጽ​ሐፍ ‘ጌታ ጌታ​ዬን በቀኜ ተቀ​መጥ፥ ጠላ​ቶ​ች​ህን ከእ​ግ​ርህ ጫማ በታች እስከ አደ​ር​ጋ​ቸው ድረስ’ ብሏል። እን​ግ​ዲህ እርሱ ራሱ ዳዊት ‘ጌታዬ’ ያለው እን​ዴት ልጁ ይሆ​ናል?” ሕዝ​ቡም ሲሰሙ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን እን​ዲህ አላ​ቸው። “ልብ​ሳ​ቸ​ውን አን​ዘ​ር​ፍ​ፈው ወዲያ ወዲህ ማለ​ትን ከሚሹ፥ በገ​በያ እጅ መነ​ሣ​ት​ንና በአ​ደ​ባ​ባይ ፊት ለፊት፥ በማ​ዕ​ድም ጊዜ በከ​በ​ሬታ መቀ​መጫ መቀ​መ​ጥን ከሚ​ወዱ ጻፎች ተጠ​በቁ። የመ​በ​ለ​ቶ​ችን ገን​ዘብ የሚ​በሉ፥ ለም​ክ​ን​ያት ጸሎ​ት​ንም የሚ​ያ​ስ​ረ​ዝሙ እነ​ዚህ ታላቅ ፍር​ድን ይቀ​በ​ላሉ።”