የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 15:11-21

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 15:11-21 አማ2000

ዳግ​መ​ኛም እን​ዲህ አለ፥ “አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበ​ሩት። ታናሹ ልጁም አባ​ቱን፦ ‘አባቴ ሆይ፥ ከገ​ን​ዘ​ብህ የሚ​ደ​ር​ሰ​ኝን ከፍ​ለህ ስጠኝ’ አለው፤ ገን​ዘ​ቡ​ንም ከፍሎ ሰጠው። ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ያ ትንሹ ልጁ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ሰብ​ስቦ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ፤ በዚ​ያም በመ​ዳ​ራት እየ​ኖረ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ በተነ፤ አጠ​ፋም። ገን​ዘ​ቡ​ንም ሁሉ በጨ​ረሰ ጊዜ፥ በዚያ ሀገር ጽኑ ራብ መጣ፤ እር​ሱም ተቸ​ገረ። ሄዶም ከዚያ ሀገር ሰዎች ለአ​ንዱ ተቀ​ጠረ፤ እሪ​ያ​ዎ​ች​ንም ይጠ​ብቅ ዘንድ ወደ እር​ሻው ቦታ ሰደ​ደው። እሪ​ያ​ዎች ከሚ​መ​ገ​ቡት ተረ​ን​ቃ​ሞም ይጠ​ግብ ዘንድ ተመኘ፤ ግን የሚ​ሰ​ጠው አል​ነ​በ​ረም። በል​ቡም እን​ዲህ ብሎ ዐሰበ፦ እህል የሚ​ተ​ር​ፋ​ቸው የአ​ባቴ ሠራ​ተ​ኞች ምን ያህል ናቸው? እኔ ግን በዚህ በረ​ኃብ ልሞት ነው። ተነ​ሥቼ ወደ አባቴ ልሂ​ድና እን​ዲህ ልበ​ለው፦ ‘አባቴ ሆይ፥ በሰ​ማ​ይም፥ በፊ​ት​ህም በደ​ልሁ። እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ ልጅህ ልባል አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እንደ አንዱ አድ​ር​ገኝ።’ ተነ​ሥ​ቶም ወደ አባቱ ሄደ፤ አባ​ቱም ከሩቅ አየ​ውና ራራ​ለት፤ ሮጦም አን​ገ​ቱን አቅፎ ሳመው። ልጁም፦ ‘አባቴ ሆይ፥ በሰ​ማ​ይም፥ በፊ​ት​ህም በደ​ልሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ልጅህ ልባል አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ነገር ግን ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እንደ አንዱ አድ​ር​ገኝ’ አለው።

Free Reading Plans and Devotionals related to የሉ​ቃስ ወን​ጌል 15:11-21