የሉ​ቃስ ወን​ጌል 12:4-7

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 12:4-7 አማ2000

ለእ​ና​ንተ ለወ​ዳ​ጆች እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ሥጋ​ች​ሁን የሚ​ገ​ድ​ሉ​ትን አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው፤ ከዚ​ህም የበ​ለጠ ማድ​ረግ የሚ​ች​ሉት የላ​ቸ​ውም። ነገር ግን፤ የም​ት​ፈ​ሩ​ትን አሳ​ያ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተስ ከገ​ደለ በኋላ ወደ ገሃ​ነም ሊጥል ሥል​ጣን ያለ​ውን ፍሩት፤ አዎ፥ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እር​ሱን ፍሩ። አም​ስት ወፎች በሁ​ለት ሻሚ መሐ​ለቅ ይሸጡ የለ​ምን? ከእ​ነ​ርሱ አን​ዲቱ ስን​ኳን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አት​ረ​ሳም። የእ​ና​ን​ተስ የራስ ጠጕ​ራ​ችሁ ሁሉ የተ​ቈ​ጠረ ነው፤ እን​ግ​ዲህ አት​ፍሩ፤ ከብዙ ወፎች እና​ንተ ትበ​ል​ጣ​ላ​ች​ሁና።