የሉ​ቃስ ወን​ጌል 11:14-32

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 11:14-32 አማ2000

ዲዳና ደን​ቆሮ ጋኔ​ን​ንም ያወጣ ነበር፤ ጋኔ​ኑም በወጣ ጊዜ ዲዳና ደን​ቆሮ የነ​በ​ረው ተና​ገረ፤ ሰዎ​ችም አደ​ነቁ። ነገር ግን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው፥ “በአ​ጋ​ን​ንት አለቃ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን ያወ​ጣ​ቸ​ዋል” ያሉ ነበሩ፤ እር​ሱም መልሶ፥ “ሰይ​ጣን ሰይ​ጣ​ንን ማው​ጣት እን​ደ​ምን ይቻ​ለ​ዋል?” አላ​ቸው። ሌሎ​ችም ሊፈ​ት​ኑት ከእ​ርሱ ዘንድ ከሰ​ማይ ምል​ክ​ትን ይፈ​ልጉ ነበር። እርሱ ግን የሚ​ያ​ስ​ቡ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እርስ በር​ስዋ የም​ት​ለ​ያይ መን​ግ​ሥት ሁሉ ትጠ​ፋ​ለች፤ ቤትም እርስ በርሱ ቢለ​ያይ ያ ቤት ይወ​ድ​ቃል። ሰይ​ጣ​ንስ እርስ በርሱ ከተ​ለ​ያየ መን​ግ​ሥቱ እን​ዴት ይጸ​ናል? በአ​ጋ​ን​ንት አለቃ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን ያወ​ጣል ትላ​ላ​ች​ሁና። እኔ በብ​ዔል ዜቡል አጋ​ን​ን​ትን የማ​ወጣ ከሆነ፥ ልጆ​ቻ​ችሁ በምን ያወ​ጡ​አ​ቸ​ዋል? ስለ​ዚህ እነ​ርሱ ይፋ​ረ​ዱ​አ​ች​ኋል። እኔ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት አጋ​ን​ን​ትን የማ​ወጣ ከሆነ እን​ግ​ዲህ አሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ወደ እና​ንተ ደር​ሳ​ለች። ኀይ​ለኛ ሰው በጦር መሣ​ሪያ ቤቱን የጠ​በቀ እንደ ሆነ ገን​ዘቡ ሁሉ ደኅና ይሆ​ናል። ከእ​ርሱ የሚ​በ​ረ​ታው ቢመ​ጣና ቢያ​ሸ​ን​ፈው ግን፥ ይታ​መ​ን​በት የነ​በ​ረ​ውን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን ይገ​ፈ​ዋል፤ የማ​ረ​ከ​ው​ንና የዘ​ረ​ፈ​ውን ገን​ዘ​ቡ​ንም ይወ​ስ​ዳል። ከእኔ ጋር ያል​ሆነ ባለ​ጋ​ራዬ ነው፤ ከእኔ ጋር የማ​ይ​ሰ​በ​ስ​ብም ይበ​ት​ን​ብ​ኛል። “ክፉ ጋኔ​ንም ከሰው በወጣ ጊዜ ውኃ ወደ​ሌ​ለ​በት ምድረ በዳ ይሄ​ዳል፤ የሚ​ያ​ር​ፍ​በ​ት​ንም መኖ​ሪያ ይሻል፤ ያላ​ገኘ እንደ ሆነም ወደ ወጣ​ሁ​በት ቤቴ እመ​ለ​ሳ​ለሁ ይላል። በመ​ጣም ጊዜ ተጠ​ርጎ አጊ​ጦም ያገ​ኘ​ዋል። ከዚ​ህም በኋላ ይሄ​ድና ከእ​ርሱ የሚ​ከፉ ሌሎች ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹን ሰባት አጋ​ን​ንት ያመ​ጣል፤ ገብ​ተ​ውም በዚያ ሰው ያድ​ሩ​በ​ታል፤ ለዚያ ሰውም ከፊ​ተ​ኛው ይልቅ የኋ​ለ​ኛው የከፋ ይሆ​ን​በ​ታል።” ከዚ​ህም በኋላ ይህን ሲና​ገር ከሕ​ዝቡ መካ​ከል አን​ዲት ሴት ድም​ፅ​ዋን አሰ​ምታ፥ “የተ​ሸ​ከ​መ​ችህ ማኅ​ፀን ብፅ​ዕት ናት፤ የጠ​ባ​ሃ​ቸው ጡቶ​ችም ብፁ​ዓት ናቸው” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “ብፁ​ዓ​ንስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ተው የሚ​ጠ​ብቁ ናቸው” አላት። ብዙ ሰዎ​ችም ተሰ​ብ​ስ​በው ሳሉ እን​ዲህ ይላ​ቸው ጀመረ ፥ “ይቺ ትው​ልድ ክፉ ናት፤ ምል​ክ​ትም ትሻ​ለች፤ ነገር ግን ከነ​ቢዩ ከዮ​ናስ ምል​ክት በቀር ምል​ክት አይ​ሰ​ጣ​ትም። ዮናስ ለነ​ነዌ ሰዎች ምል​ክት እንደ ሆና​ቸው የሰው ልጅም ለዚች ትው​ልድ እን​ዲሁ ምል​ክት ይሆ​ና​ታል። የአ​ዜብ ንግ​ሥት በፍ​ርድ ቀን ከዚች ትው​ልድ ጋር ተነ​ሥታ ትፋ​ረ​ዳ​ቸ​ዋ​ለች፤ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ጥበብ ልት​ሰማ ከም​ድር ዳርቻ መጥ​ታ​ለ​ችና፤ እነሆ፥ ከሰ​ሎ​ሞን የሚ​በ​ልጥ በዚህ አለ። የነ​ነዌ ሰዎች በፍ​ርድ ቀን ከዚች ትው​ልድ ጋር ተነ​ሥ​ተው ይፋ​ረ​ዱ​አ​ታል፤ ያሳ​ፍ​ሩ​አ​ታ​ልም፤ ዮናስ በሰ​በ​ከ​ላ​ቸው ጊዜ ንስሓ ገብ​ተ​ዋ​ልና፤ እነሆ፥ ከዮ​ናስ የሚ​በ​ልጥ በዚህ አለ።