የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘሌ​ዋ​ው​ያን 19

19
የቅ​ድ​ስ​ናና የፍ​ትሕ ሕግ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 2“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እን​ዲህ በላ​ቸው፦ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ቅዱስ ነኝና እና​ንተ ቅዱ​ሳን ሁኑ። 3ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይፍራ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ። 4ጣዖ​ታ​ት​ንም አት​ከ​ተሉ፤ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም የአ​ማ​ል​ክት ምስ​ሎች ለእ​ና​ንተ አታ​ድ​ርጉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።
5“የድ​ኅ​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስት​ሠዉ ንጹሕ አድ​ር​ጋ​ችሁ ሠዉት። 6በም​ት​ሠ​ዉ​በት ቀንና በነ​ጋው ይበ​ላል፤ እስከ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ድረስ ቢተ​ርፍ በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላል። 7በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ቢበላ ጸያፍ ነው፤ ተቀ​ባ​ይ​ነት የለ​ውም፤ 8የበ​ላ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር አር​ክ​ሶ​አ​ልና ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል፤ ያም ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።
9“የም​ድ​ራ​ች​ሁ​ንም መከር በሰ​በ​ሰ​ባ​ችሁ ጊዜ የእ​ር​ሻ​ች​ሁን አጨዳ አታ​ጥሩ፤ ስታ​ጭ​ዱም የወ​ደ​ቀ​ውን ቃር​ሚያ አት​ል​ቀሙ። 10የወ​ይ​ን​ህን ቃር​ሚያ አጥ​ር​ተህ አት​ቃ​ርም፤ የወ​ደ​ቀ​ው​ንም የወ​ይ​ን​ህን ፍሬ አት​ሰ​ብ​ስብ፤ ለድ​ሆ​ችና ለእ​ን​ግ​ዶች ተወው፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።
11“አት​ስ​ረቁ፤ አት​ዋ​ሹም፤ ባል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም የሚ​ቀማ አይ​ኑር።#ዕብ. “ከእ​ና​ን​ተም እርስ በእ​ር​ሳ​ችሁ አት​ነ​ቃ​ቀፉ” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “ባል​ን​ጀ​ራ​ውን በመ​ቃ​ወም የሐ​ሰት ምስ​ክር አይ​ሁን” ይላል። 12በስ​ሜም በሐ​ሰት አት​ማሉ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ቅዱስ ስም አታ​ር​ክሱ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።
13“በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ግፍ አታ​ድ​ርግ፤ አት​ቀ​ማ​ውም። የሞ​ያ​ተ​ኛው ዋጋ እስከ ነገ ድረስ በአ​ንተ ዘንድ አይ​ደ​ር​ብህ። 14ደን​ቆ​ሮ​ውን አት​ስ​ደብ፤ በዕ​ው​ርም ፊት ዕን​ቅ​ፋት አታ​ድ​ርግ፤ ነገር ግን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።
15“በፍ​ርድ ዐመፃ አታ​ድ​ርጉ፤ ለድሃ አታ​ድላ፤ ባለ​ጠ​ጋ​ው​ንም አታ​ክ​ብር፤ ነገር ግን ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ በእ​ው​ነት ፍረድ። 16በሕ​ዝ​ብህ መካ​ከል በሸ​ን​ጋ​ይ​ነት አት​ዙር፤ በባ​ል​ን​ጀ​ራ​ህም ደም ላይ#ግእዙ “በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ነፍስ ላይ” ይላል። አት​ቁም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝ።
17“ወን​ድ​ም​ህን አት​በ​ድ​ለው፤ በል​ብ​ህም አት​ጥ​ላው፤ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት ኀጢ​አት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብህ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን የም​ት​ነ​ቅ​ፍ​በ​ትን ንገ​ረው፤ ገሥ​ጸ​ውም። 18አት​በ​ቀል፤ በሕ​ዝ​ብ​ህም ልጆች ቂም አት​ያዝ፤ ነገር ግን ባል​ን​ጀ​ራ​ህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝና።
19“ሥር​ዐ​ቴን ጠብቁ፤ በበ​ሬህ በባ​ዕድ ቀን​በር አት​ረስ፤ በወ​ይን ቦታህ የተ​ለ​ያየ ዘር አት​ዝራ፤ ከሁ​ለት ዐይ​ነት ነገር የተ​ሠራ ልብስ ኀፍ​ረት ነውና አት​ል​በስ።
20“ማና​ቸ​ውም ሰው ከሴት ባሪያ ጋር ቢተኛ፥ እር​ስ​ዋም ለባል የተ​ሰ​ጠች፥ ዋጋ​ዋም ያል​ተ​ከ​ፈለ፥ አር​ነት ያል​ወ​ጣች ብት​ሆን፥ ቅጣት አለ​ባ​ቸው፤ አር​ነት አል​ወ​ጣ​ች​ምና አይ​ገ​ደ​ሉም። 21እር​ሱም የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕት አውራ በግ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ያመ​ጣል። 22ካህ​ኑም ስለ ሠራው ኀጢ​አት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት በግ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ የሠ​ራ​ውም ኀጢ​አት ይቀ​ር​ለ​ታል።
23“አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ የሚ​በላ የፍሬ ዛፍ ሁሉ በተ​ከ​ላ​ች​ሁም ጊዜ ከር​ኵ​ሰቱ ሁሉ ታጠ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ፤ የሦ​ስቱ ዓመት ፍሬም ርኩስ ነው፤ አይ​በ​ላም። 24በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ፍሬ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ቅዱስ ይሁን። 25በአ​ም​ስ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ፍሬ​ውን ብሉ፤ ፍሬ​ውም ይበ​ዛ​ላ​ች​ኋል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።
26“በተ​ራራ ላይ አት​ብሉ፤ አት​ር​ከሱ፥#ዕብ. “ከደሙ ጋር ምንም አት​ብሉ ፤ አስ​ማ​ትም አታ​ድ​ርጉ” ይላል። በወ​ፍም አታ​ሟ​ርቱ። 27የራስ ጠጕ​ራ​ች​ሁ​ንም ዙሪ​ያ​ውን አት​ከ​ር​ክ​ሙት፤ ጢማ​ች​ሁ​ንም አት​ላጩ። 28ሰው ቢሞት ምላጭ ወደ ሥጋ​ችሁ አታ​ቅ​ርቡ፤ ገላ​ች​ሁ​ንም አት​ን​ቀ​ሱት፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።
29“ምድ​ሪቱ ከግ​ል​ሙ​ትና፥ ከር​ኵ​ሰ​ትም እን​ዳ​ት​ሞላ ሴት ልጅ​ህን ታመ​ነ​ዝር ዘንድ አታ​ር​ክ​ሳት። 30ሰን​በ​ታ​ቴን ጠብቁ፤ መቅ​ደ​ሴ​ንም አክ​ብሩ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።
31“ወደ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ችና ወደ ጠን​ቋ​ዮች አት​ሂዱ፤ እን​ዳ​ት​ረ​ክ​ሱ​ባ​ቸ​ውም አት​ፈ​ል​ጉ​አ​ቸው፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።
32“በሽ​በ​ታሙ ፊት ተነሣ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንም አክ​ብር፤ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ፍራ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።
33“በሀ​ገ​ራ​ችሁ ውስጥ እን​ግዳ ከእ​ና​ንተ ጋር ቢቀ​መጥ ግፍ አታ​ድ​ር​ጉ​በት። 34እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር እን​ግ​ዶች ነበ​ራ​ች​ሁና፤ ወደ እና​ንተ የመጣ እን​ግዳ እንደ ሀገር ልጅ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ እር​ሱን እንደ ራሳ​ችሁ ውደ​ዱት፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።
35“በፍ​ርድ፥ በመ​ለ​ካ​ትም፥ በመ​መ​ዘ​ንም፥ በመ​ስ​ፈ​ርም ዐመፃ አታ​ድ​ርጉ። 36የእ​ው​ነ​ትም ሚዛን፥ የእ​ው​ነ​ትም መመ​ዘኛ፥#ዕብ. “የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ” የሚል ይጨ​ም​ራል። የእ​ው​ነ​ትም የፈ​ሳሽ መስ​ፈ​ሪያ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እኔ ነኝ። 37ሕጌን ሁሉ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ሁሉ ጠብቁ፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ