ሜም። “እግዚአብሔር ያላዘዘው ይመጣል፥ ከልዑል አፍም ያልወጣ መልካም ወይም ክፉ ይሆናል” የሚል ማን ነው? ሰው ሕያው ሲሆን ስለ ኀጢአቱ ለምን ያጕረመርማል? ኖን። መንገዳችንን እንመርምርና እንፈትን፤ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ። ልባችንን ከእጃችን ጋር ወደ እግዚአብሔር ወደ ሰማይ እናንሣ። በድለናል፤ ዐምፀናልም፤ አንተም አልራራህልንም። ሳምኬት። በቍጣህ ከደንኸን፤ አሳደድኸንም፤ ገደልኸን፤ አልራራህልንም። ጸሎታችን እንዳያርግ ራስህን በደመና ከደንህ። እንድናዝንና እንዳናይም በአሕዛብ መካከል አስቀመጥኸን። ዔ። ጠላቶቻችን ሁሉ በእኛ ላይ አፋቸውን ከፈቱ። ፍርሀትና ቍጣ፥ ጥፋትና ቅጥቃጤ ያዘን። ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ከዐይኔ የውኃ ጐርፍ ፈሰሰ። ፌ። ዐይኔ ተደፈነች፤ እንግዲህ ከማንጋጠጥ ዝም አልልም። እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ እስኪመለከት ድረስ። ስለ ከተማዬ ቈነጃጅት ሁሉ ዐይኔ ነፍሴን አሳዘነች። ጻዴ። በከንቱ ነገር ጠላቶች ሁሉ እንደ ወፍ ማደንን አደኑኝ። ጠላቶች ሕይወቴን በጕድጓድ አጠፉ፤ በላዬም ድንጋይ ገጠሙ። በራሴ ላይ ውኃ ተከነበለ፤ እኔም፥ “ጠፋሁ” ብዬ ነበር። ቆፍ። አቤቱ፥ በጥልቅ ጕድጓድ ውስጥ ሆኜ ስምህን ጠራሁ። አንተ ድምፄን ሰማህ፤ ጆሮህንም ከልመናዬ አትመልስ። በጠራሁህ ቀን ወደ እኔ ቅረብ፤ “አትፍራም” በለኝ። ሬስ። አቤቱ፥ የነፍሴን ፍርድ ፈረድህ፤ ሕይወቴንም ተቤዥህ። አቤቱ፥ ጭንቀቴን አይተሃል፤ ፍርዴን ፍረድልኝ። በቀላቸውን ሁሉና በእኔ ላይ ያለውን ዐሳባቸውን ሁሉ አየህ። ሣን። አቤቱ፥ ስድባቸውንና በእኔ ላይ ያለውን ዐሳባቸውን ሁሉ ሰማህ። የተነሡብኝን ሰዎች ከንፈሮች ቀኑንም ሁሉ ያሰቡብኝን ዐሳባቸውን ሰማህ። መቀመጣቸውንና መነሣታቸውን ተመልከት፤ እኔ መዝፈኛቸው ነኝ። ታው። አቤቱ፥ እንደ እጃቸው ሥራ ፍዳቸውን ክፈላቸው። የልብ ሕማምንና ርግማንህን ስጣቸው። አቤቱ፥ እንደ ልባቸው ክፋት በቍጣህ ታሳድዳቸዋለህ፤ ከሰማይም በታች ታጠፋቸዋለህ።
ሰቆቃወ ኤርምያስ ነቢይ 3 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሰቆቃወ ኤርምያስ ነቢይ 3:37-66
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች