የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 3:7-13

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 3:7-13 አማ2000

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እን​ዲሁ ከአ​ንተ ጋር መሆ​ኔን ያውቁ ዘንድ በዚህ ቀን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደ​ር​ግህ ዘንድ እጀ​ም​ራ​ለሁ። አሁ​ንም አንተ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የሚ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ዳር ስት​ደ​ርሱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውስጥ ቁሙ ብለህ እዘዝ” አለው። ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ “ወደ​ዚህ ቀር​ባ​ችሁ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ” አለ። ኢያ​ሱም አለ፥ “ሕያው አም​ላክ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እንደ ሆነ፥ እር​ሱም ከፊ​ታ​ችሁ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውን፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ፈጽሞ እን​ዲ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው በዚህ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። እነሆ፥ የም​ድር ሁሉ ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት በፊ​ታ​ችሁ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ለች። አሁ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ዐሥራ ሁለት ሰዎ​ችን ምረጡ፤ ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሰው ይሁን። እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የም​ድ​ርን ሁሉ ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግር ጫማ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ የዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ይደ​ር​ቃል፤ ከላይ የሚ​ወ​ር​ደ​ውም ውኃ ይቆ​ማል።”