የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1

1
የከ​ነ​ዓን ድል መሆን
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሙ​ሴን አገ​ል​ጋይ የነ​ዌን ልጅ ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 2“አገ​ል​ጋዬ ሙሴ ሞቶ​አል፤ አሁ​ንም አን​ተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ​ም​ሰ​ጣ​ቸው ምድር ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ። 3ለሙሴ እንደ ነገ​ር​ሁት የእ​ግ​ራ​ችሁ ጫማ የሚ​ረ​ግ​ጠ​ውን ቦታ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ሰጥ​ቼ​አ​ለሁ። 4ከሊ​ባ​ኖስ ፊት ለፊት ምድረ በዳ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ድረስ የኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን ምድር ሁሉ#“የኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን ምድር ሁሉ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም እስከ ፀሐይ መግ​ቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ወሰ​ና​ችሁ ይሆ​ናል። 5በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ የሚ​ቋ​ቋ​ምህ የለም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበ​ርሁ እን​ዲሁ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ አል​ጥ​ል​ህም፥ ቸልም አል​ል​ህም። 6ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን ምድር ለዚህ ሕዝብ ታወ​ር​ሳ​ለ​ህና ጽና፥ በርታ። 7አገ​ል​ጋዬ ሙሴ እንደ አዘ​ዘህ ሕግን ሁሉ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ ጽና፤ እጅ​ግም በርታ፤ ሁሉን እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​ሠራ ታውቅ ዘንድ ከእ​ርሱ ወደ ቀኝ ወደ ግራም አት​በል። 8የዚህ ሕግ መጽ​ሐፍ ከአ​ፍህ አይ​ለይ፤ ነገር ግን የተ​ጻ​ፈ​በ​ትን ሁሉ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ በቀ​ንም በሌ​ሊ​ትም አን​ብ​በው፤ የዚ​ያን ጊዜም መን​ገ​ድህ ይቀ​ና​ል​ሃል፤ አስ​ተ​ዋ​ይም ትሆ​ና​ለህ። 9እነሆ አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ድ​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና ጽና፥ በርታ፤ አት​ፍራ፥ አት​ደ​ን​ግ​ጥም።”
10ኢያ​ሱም የሕ​ዝ​ቡን ጻፎች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፦ 11“በሰ​ፈሩ መካ​ከል ዕለፉ፥ ሕዝ​ቡ​ንም፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር እስከ ሦስት ቀን ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ልት​ወ​ር​ሱ​አት ትገ​ቡ​ባ​ታ​ላ​ች​ሁና ስን​ቃ​ች​ሁን አዘ​ጋጁ ብላ​ችሁ እዘ​ዙ​አ​ቸው።”
12ኢያ​ሱም ሮቤ​ል​ንና ጋድን#ዕብ. “የሮ​ቤ​ልን ልጆ​ችና የጋ​ድን ልጆች” ይላል። የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ 13“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ እን​ዲህ ብሎ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ቃል አስቡ፦ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሳ​ር​ፋ​ች​ኋል፤ ይህ​ች​ንም ምድር ይሰ​ጣ​ች​ኋል። 14ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁና ልጆ​ቻ​ችሁ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሙሴ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሰ​ጣ​ችሁ በዚች ምድር ይቀ​መጡ፤ እና​ንተ፥ ጽኑ​ዓን ሁሉ ግን ታጥ​ቃ​ችሁ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ፊት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ተዋ​ጉ​ላ​ቸው። 15አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ እና​ንተ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን እስ​ኪ​ያ​ሳ​ርፍ ድረስ፥ እነ​ር​ሱም ደግሞ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ምድር እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ፤ ከዚ​ያም በኋላ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ በፀ​ሐይ መውጫ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሰጣ​ችሁ ወደ ርስ​ታ​ችሁ ምድር ትገ​ባ​ላ​ችሁ፤ ትወ​ር​ሱ​አ​ት​ማ​ላ​ችሁ።” 16እነ​ር​ሱም ለኢ​ያሱ እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ለት፥ “ያዘ​ዝ​ኸ​ንን ነገር ሁሉ እና​ደ​ር​ጋ​ለን ወደ​ም​ት​ል​ከ​ንም ስፍራ እን​ሄ​ዳ​ለን። 17በሁ​ሉም ለሙሴ እንደ ታዘ​ዝን እን​ዲሁ ለአ​ንተ ደግሞ እን​ታ​ዘ​ዛ​ለን፤ ብቻ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአ​ንተ ጋር ይሁን። 18ለአ​ንተ የማ​ይ​ታ​ዘዝ፥ የም​ታ​ዝ​ዘ​ው​ንም ቃል የማ​ይ​ሰማ ሁሉ፥ እርሱ ይገ​ደል፤ አሁ​ንም ጽና፥ በርታ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}