የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ዮናስ 3:3-10

ትን​ቢተ ዮናስ 3:3-10 አማ2000

ዮና​ስም ተነ​ሥቶ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነ​ዌም ታላቅ ከተማ ነበ​ረች፤ የቅ​ጥ​ር​ዋም ዙሪያ በእ​ግር የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ያህል ነበረ። ዮና​ስም የአ​ንድ ቀን መን​ገድ ያህል ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፥ “በሦ​ስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገ​ለ​በ​ጣ​ለች አለ።” የነ​ነዌ ሰዎ​ችም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመኑ፤ ለጾም ዐዋጅ ነገሩ፤ ከታ​ላ​ቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ። ወሬ​ውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እር​ሱም ከዙ​ፋኑ ተነ​ሥቶ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን አወ​ለቀ፤ ማቅም ለበሰ፤ በአ​መ​ድም ላይ ተቀ​መጠ። ዐዋ​ጅም አስ​ነ​ገረ፤ በነ​ነ​ዌም ውስጥ የን​ጉ​ሡ​ንና የመ​ኳ​ን​ን​ቱን ትእ​ዛዝ አሳ​ወጀ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ሰዎ​ችና እን​ስ​ሶች፥ ላሞ​ችና በጎች አን​ዳች አይ​ቅ​መሱ፤ አይ​ሰ​ማ​ሩም፤ ውኃ​ንም አይ​ጠጡ፤ ሰዎ​ችና እን​ስ​ሶ​ችም ማቅ ይል​በሱ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ን​ድ​ነት ይጩኹ፤ ሰዎ​ችም ሁሉ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውና በእ​ጃ​ቸው ከአ​ለው ግፍ ይመ​ለሱ። እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ይምራን፥ ከጽኑ ቁጣውም ይመለስ እንደሆነ ማን ያውቃል?” እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ ከተናገረው ክፉ ነገር ተመለሰ፤ አላደረገውምም።