የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ዮናስ 1

1
ዮናስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለ​መ​ታ​ዘዙ
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“ተነ​ሥ​ተህ ወደ ታላ​ቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የክ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ጩኸት ወደ ፊቴ ወጥ​ቶ​አ​ልና ለእ​ነ​ርሱ ስበክ።” 3ዮናስ ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ተር​ሴስ ይሸሽ ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮ​ጴም ወረደ፤ ወደ ተር​ሴ​ስም የም​ታ​ልፍ መር​ከብ አገኘ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ኰብ​ልሎ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወደ ተር​ሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እር​ስዋ ገባ።
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሕሩ ላይ ታላቅ ነፋ​ስን አመጣ፤ በባ​ሕ​ሩም ላይ ታላቅ ማዕ​በል ሆነ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም ልት​ሰ​በር ቀረ​በች። 5መር​ከ​በ​ኞ​ቹም ፈሩ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ አም​ላኩ ጮኸ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም እን​ድ​ት​ቀ​ል​ል​ላ​ቸው በው​ስ​ጥዋ የነ​በ​ረ​ውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መር​ከቡ ውስ​ጠ​ኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ ተኝ​ቶም ያን​ኳ​ርፍ ነበር። 6የመ​ር​ከ​ቡም አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ምነው ተኝ​ተ​ሃል? እን​ዳ​ን​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ነን ዘንድ ተነ​ሥ​ተህ አም​ላ​ክ​ህን ጥራ” አለው። 7እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክ​ን​ያት እንደ አገ​ኘን እና​ውቅ ዘንድ ኑ፤ ዕጣ እን​ጣ​ጣል” ተባ​ባሉ። ዕጣም ተጣ​ጣሉ፤ ዕጣ​ውም በዮ​ናስ ላይ ወደቀ። 8የዚ​ያን ጊዜም፥ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክ​ን​ያት እን​ዳ​ገ​ኘን እባ​ክህ ንገ​ረን፤ ሥራህ ምን​ድን ነው? ከወ​ዴ​ትስ መጣህ? ወዴ​ትስ ትሄ​ዳ​ለህ? ሀገ​ርህ የት ነው? ወገ​ን​ህስ ምን​ድን ነው?” አሉት። 9እር​ሱም፥ “እኔ ዕብ​ራዊ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ነኝ፤ ባሕ​ሩ​ንና የብ​ሱን የፈ​ጠ​ረ​ውን የሰ​ማ​ይን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ል​ካ​ለሁ” አላ​ቸው። 10እነ​ዚ​ያም ሰዎች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ኰበ​ለለ እርሱ ስለ ነገ​ራ​ቸው ዐው​ቀ​ዋ​ልና እጅግ ፈር​ተው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ምን​ድን ነው?” አሉት።
11ባሕሩ ይታ​ወክ ነበ​ርና፥ ታላቅ ማዕ​በ​ልም ተነ​ሥቶ ነበ​ርና፥ “ባሕሩ ጸጥ ይል​ልን ዘንድ እን​ግ​ዲህ ምን እና​ድ​ር​ግህ?” አሉት። 12እር​ሱም፥ “ይህ ታላቅ ማዕ​በል በእኔ ምክ​ን​ያት እንደ አገ​ኛ​ችሁ ዐው​ቃ​ለ​ሁና አን​ሥ​ታ​ችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ፤ ባሕ​ሩም ጽጥ ይል​ላ​ች​ኋል” አላ​ቸው። 13ሰዎቹ ግን ወደ ምድሩ ሊመ​ለሱ አጥ​ብ​ቀው ቀዘፉ፤ ዳሩ ግን ባሕሩ እጅግ አብ​ዝቶ ይና​ወ​ጥ​ባ​ቸው ነበ​ርና አል​ቻ​ሉም። 14ሁሉም አንድ ሆነው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ “አቤቱ! አንተ እንደ ወደ​ድህ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ስለ​ዚህ ሰው ነፍስ አታ​ጥ​ፋን፤ ንጹሕ ደም​ንም አታ​ድ​ር​ግ​ብን።” አሉ። 15ዮና​ስ​ንም ወስ​ደው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕ​ሩም ከመ​ና​ወጡ ጸጥ አለ። 16ሰዎ​ቹም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጅግ ፈሩ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ፤ ስእ​ለ​ት​ንም ተሳሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ