መጽሐፈ ኢዮብ 39
39
1“ዋልያ#ግሪኩ እና ዕብ. “ብሆር” ይላል። የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን?
# ግሪኩ “ዋልያ” የሚል ይጨምራል። የምታምጥበትንስ ጊዜ ትመለከታለህን?
2እርስዋ የምትወልድበትንስ ሙሉ ወራት ትቈጥራለህን?
ከምጥስ ትገላግላታለህን?
3ልጆቻቸውንስ ያለ ፍርሃት አሳድገሃልን?
መከራቸውንስ አስወግደሃልን?
4ልጆቻቸው ያመልጣሉ።#ዕብ. “ይጠነክራሉ” ይላል።
ይባዛሉ፥ ይዋለዳሉም።
ይወጣሉ፥ ወደ እነርሱም አይመለሱም።
5“የሜዳውንስ አህያ ነጻነት ማን አወጣው?
ከእስራቱስ ማን ፈታው?
6በረሃውን ለእርሱ ቤት፥
መኖሪያውንም በጨው ምድር አድርጌ ሰጠሁት።
7በከተማው ሕዝብ ውካታ ይዘብታል፤
የሚያስፈራውንም ጩኸት አይሰማም።
8ተራራውን እንደ መሰምሪያው ይመለከተዋል፥
ለምለሙንም ሁሉ ይፈልጋል።
9“ጎሽ ያገለግልህ ዘንድ ይፈቅዳልን?
ወይስ በግርግምህ አጠገብ ያድራልን?
10በቀንበር ትጠምደዋለህን?
በእርሻህስ ውስጥ ትልም ያርስልሃልን?
11ጕልበቱስ ብርቱ ስለሆነ ትታመነዋለህን?
ተግባርህንስ ለእርሱ ትተዋለህን?
12ዘርህንስ ይመልስልህ ዘንድ፥
በአውድማህስ ያከማችልህ ዘንድ ትታመነዋለህን?
13“ሰጎን ክንፍዋን በደስታ ታንቀሳቅሳለች፥
በፀነሰችም ጊዜ ልትበላ ትመኛለች፥#በግሪክ ሰባ. ሊ. ይለያል።
14ዕንቍላልን በመሬት ላይ ትጥላለች፥
በአፈርም ውስጥ ታሞቀዋለች፥#በግእዝ ይለያል።
15እግር ይሰብረው ዘንድ፥
የምድረ በዳም አውሬ ይረግጠው ዘንድ ትረሳለች።
16የእርስዋ እንዳልሆኑ በልጆችዋ ላይ ትጨክናለች፤#በግእዝ ይለያል።
ያለ ፍርሀትም በከንቱ ትሠራለች፤
17እግዚአብሔር ጥበብን ከእርስዋ ከልክሎአልና፥#ግእዙ በአወንታ ነው።
ማስተዋልንም አልሰጣትምና።
18በዘመንዋ ወደ ላይ ራስዋን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፥
በፈረሱና በፈረሰኛው ትሣለቃለች።
19“ለፈረስ አንተ ጕልበቱን ሰጥተኸዋልን?
አንገቱንስ ጋማ አልብሰኸዋልን?
20በፍጹም የጦር መሣሪያ አስጊጠኸዋልን?
እምቢያውንስ በብርታት የከበረ አድርገኸዋልን?
21በኮቴው በሸለቆው ውስጥ ይጐደፍራል፥
በጕልበቱም ወደ ሜዳ ይወጣል።
22በሚገናኘው ፍላጻ ላይ ይስቃል።
ከሰይፍም ፊት አይመለስም።
23ቀስትና ጦር በእርሱ ላይ ይበረታሉ፥
24በቍጣውም መሬትን ያጠፋል፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ይወጣል” ይላል።
የመለከትም ድምፅ እስከሚሰማው አያምንም።
25የመለከትም ድምፅ ሲሰማ፦ እሰይ ይላል፤
ከሩቅም ሆኖ ሰልፍንና የአለቆችን ጩኸት፥
የሠራዊቱንም ውካታ ያሸታል።
26“በውኑ ከጥበብህ የተነሣ ጭልፊት ያንዣብባልን?
ወይስ ክንፎቹን ወደ ደቡብ ይዘረጋልን?
27በአፍህ ትእዛዝ ንስር ከፍ ከፍ ይላልን?
ጆፌ አሞራስ ልጆቹን አቅፎ ያድራልን?
28በዓለቱ ገደል ላይ ይኖራል፤
በገደሉ ገመገምና በጥጉ ያድራል።
29በዚያም ሆኖ የሚበላውን ይፈልጋል፤
ዐይኖቹም በሩቁ ይመለከታሉ።
30ጫጭቶቹም ወደ ደም ይሮጣሉ፥
በድን ወደ አለበትም ስፍራ ወዲያውኑ ይደርሳሉ።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 39: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ