የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 5:1-29

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 5:1-29 አማ2000

ከዚ​ህም በኋላ በአ​ይ​ሁድ በዓል እን​ዲህ ሆነ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በበ​ጎች በር አጠ​ገብ መጠ​መ​ቂያ ነበ​ረች፤ ስም​ዋ​ንም በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉ​አ​ታል፤ አም​ስት እር​ከ​ኖ​ችም ነበ​ሩ​አት። በዚ​ያም ዕው​ሮ​ችና አን​ካ​ሶች፥ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም የሰ​ለለ ብዙ ድው​ያን ተኝ​ተው የው​ኃ​ዉን መና​ወጥ ይጠ​ባ​በቁ ነበር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ወደ መጠ​መ​ቂ​ያዉ ወርዶ ውኃ​ዉን በሚ​ያ​ና​ው​ጠው ጊዜ፥ ከው​ኃዉ መና​ወጥ በኋላ በመ​ጀ​መ​ሪያ ወርዶ የሚ​ጠ​መቅ ካለ​በት ደዌ ሁሉ ይፈ​ወስ ነበ​ርና። በዚ​ያም ከታ​መመ ሠላሳ ስም​ንት ዓመት የሆ​ነው አንድ ሰው ነበር። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን ሰው በአ​ል​ጋዉ ተኝቶ ባየ ጊዜ በደዌ ብዙ ዘመን እንደ ቈየ ዐውቆ፥ “ልት​ድን ትወ​ዳ​ለ​ህን?” አለው። ድው​ዩም መልሶ፥ “አዎን ጌታዬ ሆይ፥ ነገር ግን ውኃዉ በተ​ና​ወጠ ጊዜ ወደ መጠ​መ​ቂ​ያዉ የሚ​ያ​ወ​ር​ደኝ ሰው የለ​ኝም፤ እኔ በም​መ​ጣ​በት ጊዜ ሌላው ቀድ​ሞኝ ይወ​ር​ዳል” አለው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ተነ​ሥና አል​ጋ​ህን ተሸ​ክ​መህ ሂድ” አለው። ወዲ​ያ​ው​ኑም ያ ሰው ድኖ አል​ጋ​ውን ተሸ​ክሞ ሄደ፤ ያች ቀንም ሰን​በት ነበ​ረች። አይ​ሁ​ድም የዳ​ነ​ውን ሰው፥ “ዛሬ ሰን​በት ነው፤ አል​ጋ​ህን ልት​ሸ​ከም አይ​ገ​ባ​ህም” አሉት። እር​ሱም መልሶ፥ “ያዳ​ነኝ እርሱ፦ አል​ጋ​ህን ተሸ​ክ​መህ ሂድ አለኝ” አላ​ቸው። አይ​ሁ​ድም፥ “አል​ጋ​ህን ተሸ​ክ​መህ ሂድ ያለህ ሰው​ዬው ማነው?” ብለው ጠየ​ቁት። ያ የተ​ፈ​ወ​ሰው ግን ያዳ​ነው ማን እንደ ሆነ አላ​ወ​ቀም፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በዚያ ቦታ በነ​በ​ሩት ብዙ ሰዎች መካ​ከል ተሰ​ውሮ ነበ​ርና። ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያን የዳ​ነ​ውን ሰው በቤተ መቅ​ደስ አገ​ኘ​ውና፥ “እነሆ፥ ድነ​ሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እን​ዳ​ያ​ገ​ኝህ ዳግ​መኛ እን​ዳ​ት​በ​ድል ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። ያም ሰው ሄዶ ያዳ​ነው ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እንደ ሆነ ለአ​ይ​ሁድ ነገ​ራ​ቸው። ስለ​ዚ​ህም አይ​ሁድ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ያሳ​ድ​ዱ​ትና ሊገ​ድ​ሉ​ትም ይሹ ነበር፤ በሰ​ን​በት እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበ​ርና። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “አባቴ እስከ ዛሬ ይሠ​ራል፤ እኔም እሠ​ራ​ለሁ” አላ​ቸው። ስለ​ዚ​ህም አይ​ሁድ ሊገ​ድ​ሉት በጣም ይፈ​ልጉ ነበር፤ “ሰን​በ​ትን የሚ​ሽር ነው” በማ​ለት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን “አባቴ ነው ይላል፤ ራሱ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ያስ​ተ​ካ​ክ​ላል” በማ​ለት ነው እንጂ። ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወልድ ከራሱ ብቻ ምንም ሊያ​ደ​ርግ አይ​ች​ልም፤ አብ ሲያ​ደ​ርግ ያየ​ውን ነው እንጂ፤ ወል​ድም አብ የሚ​ሠ​ራ​ውን ያንኑ እን​ዲሁ ይሠ​ራል። አብ ልጁን ይወ​ዳ​ልና የሚ​ሠ​ራ​ው​ንም ሥራ ሁሉ ያሳ​የ​ዋል፤ እና​ን​ተም ታደ​ንቁ ዘንድ ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ሥራን ያሳ​የ​ዋል። አብ ሙታ​ንን እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው፥ ሕይ​ወ​ት​ንም እን​ደ​ሚ​ሰ​ጣ​ቸው እን​ዲሁ ወል​ድም ለሚ​ወ​ድ​ዳ​ቸው ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣል። አብ ከቶ በማ​ንም አይ​ፈ​ር​ድም፤ ፍር​ዱን ሁሉ ለወ​ልድ ሰጠው እንጂ። ሰዎች ሁሉ አብን እን​ደ​ሚ​ያ​ከ​ብሩ ወል​ድን ያከ​ብሩ ዘንድ፤ ወል​ድን የማ​ያ​ከ​ብር ግን የላ​ከ​ውን አብን አያ​ከ​ብ​ርም። እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቃሌን የሚ​ሰማ በላ​ከ​ኝም የሚ​ያ​ምን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ያገ​ኛል፤ ከሞ​ትም ወደ ሕይ​ወት ተሻ​ገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይ​ሄ​ድም። “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሙታን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ ቃል የሚ​ሰ​ሙ​በት ሰዓት ይመ​ጣል፤ እር​ሱም አሁን ነው፤ የሚ​ሰ​ሙ​ትም ይድ​ናሉ። ለአብ በራሱ ሕይ​ወት እን​ዳ​ለው፥ እን​ዲ​ሁም ደግሞ ለወ​ልድ በራሱ ሕይ​ወት እን​ዲ​ኖ​ረው ሰጠው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ የሰው ልጅ ነውና ይፈ​ርድ ዘንድ ሥል​ጣ​ንን ሰጠው። “በመ​ቃ​ብር ያሉ ሁሉ ቃሉን የሚ​ሰ​ሙ​ባት ጊዜ ትመ​ጣ​ለ​ችና ስለ​ዚህ አታ​ድ​ንቁ። መል​ካም የሠሩ ለሕ​ይ​ወት ትን​ሣኤ፥ ክፉ የሠ​ሩም ለፍ​ርድ ትን​ሣኤ ይነ​ሣሉ።

Free Reading Plans and Devotionals related to የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 5:1-29