የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 4:11-15

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 4:11-15 አማ2000

ያቺ ሴትም እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ መቅጃ እንኳ የለ​ህም፤ ጕድ​ጓ​ዱም ጥልቅ ነው፤ እን​ግ​ዲህ የሕ​ይ​ወት ውኃ ከወ​ዴት ታገ​ኛ​ለህ? ይህን ጕድ​ጓድ ከሰ​ጠን ከአ​ባ​ታ​ችን ከያ​ዕ​ቆብ አንተ ትበ​ል​ጣ​ለ​ህን? እር​ሱም ልጆ​ቹም፥ ከብ​ቶ​ቹም ከእ​ርሱ ጠጥ​ተ​ዋል።” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “ከዚህ ውኃ የሚ​ጠጣ ሁሉ ዳግ​መኛ ይጠ​ማል። እኔ ከም​ሰ​ጠው ውኃ የሚ​ጠጣ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም፤ እኔ የም​ሰ​ጠው ውኃ በው​ስጡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የሚ​ፈ​ልቅ የውኃ ምንጭ ይሆ​ን​ለ​ታል እንጂ።” ሴቲ​ቱም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እን​ዳ​ል​ጠማ፥ ዳግ​መ​ኛም ውኃ ልቀዳ ወደ​ዚህ እን​ዳ​ል​መጣ እባ​ክህ ከዚህ ውኃ ስጠኝ፤” አለ​ችው።