የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 4:1-15

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 4:1-15 አማ2000

ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከዮ​ሐ​ንስ ይልቅ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን እንደ አበ​ዛና እን​ደ​ሚ​ያ​ጠ​ምቅ ፈሪ​ሳ​ው​ያን መስ​ማ​ታ​ቸ​ውን ዐወቀ። ነገር ግን ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እንጂ እርሱ ራሱ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ አላ​ጠ​መ​ቀም። የይ​ሁ​ዳ​ንም ምድር ትቶ ዳግ​መኛ ወደ ገሊላ ሄደ። በሰ​ማ​ርያ በኩ​ልም ሲያ​ልፍ ሳለ፥ ያዕ​ቆብ ለልጁ ለዮ​ሴፍ በሰ​ጠው በወ​ይን ቦታ አቅ​ራ​ቢያ ወደ አለ​ችው ሲካር ወደ​ም​ት​ባ​ለው የሰ​ማ​ርያ ከተማ ደረሰ። በዚ​ያም የያ​ዕ​ቆብ የውኃ ጕድ​ጓድ ነበረ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መን​ገድ በመ​ሄድ ደክሞ በዚያ ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ተቀ​መጠ፤ ጊዜ​ውም ስድ​ስት ሰዓት ያህል ነበር። እነሆ፥ ከሰ​ማ​ርያ አን​ዲት ሴት ውኃ ልት​ቀዳ መጣች፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ውኃ አጠ​ጪኝ” አላት። ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበ​ርና። ያቺ የሰ​ማ​ርያ ሴትም፥ “አንተ አይ​ሁ​ዳዊ ስት​ሆን፥ እኔም ሳም​ራ​ዊት ስሆን እን​ዴት ከእኔ ዘንድ ውኃ ልት​ጠጣ ትለ​ም​ና​ለህ?” አለ​ችው፤ አይ​ሁድ ከሳ​ም​ራ​ው​ያን ጋር በሥ​ር​ዐት አይ​ተ​ባ​በ​ሩም ነበ​ርና። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦ​ታና ውኃ አጠ​ጪኝ ብሎ የሚ​ለ​ም​ንሽ ማን እንደ ሆነ ብታ​ው​ቂስ አንቺ ደግሞ በለ​መ​ን​ሺው ነበር፤ እር​ሱም የሕ​ይ​ወ​ትን ውኃ በሰ​ጠሽ ነበር” ብሎ መለ​ሰ​ላት። ያቺ ሴትም እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ መቅጃ እንኳ የለ​ህም፤ ጕድ​ጓ​ዱም ጥልቅ ነው፤ እን​ግ​ዲህ የሕ​ይ​ወት ውኃ ከወ​ዴት ታገ​ኛ​ለህ? ይህን ጕድ​ጓድ ከሰ​ጠን ከአ​ባ​ታ​ችን ከያ​ዕ​ቆብ አንተ ትበ​ል​ጣ​ለ​ህን? እር​ሱም ልጆ​ቹም፥ ከብ​ቶ​ቹም ከእ​ርሱ ጠጥ​ተ​ዋል።” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላት፥ “ከዚህ ውኃ የሚ​ጠጣ ሁሉ ዳግ​መኛ ይጠ​ማል። እኔ ከም​ሰ​ጠው ውኃ የሚ​ጠጣ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም፤ እኔ የም​ሰ​ጠው ውኃ በው​ስጡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የሚ​ፈ​ልቅ የውኃ ምንጭ ይሆ​ን​ለ​ታል እንጂ።” ሴቲ​ቱም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እን​ዳ​ል​ጠማ፥ ዳግ​መ​ኛም ውኃ ልቀዳ ወደ​ዚህ እን​ዳ​ል​መጣ እባ​ክህ ከዚህ ውኃ ስጠኝ፤” አለ​ችው።