ምሳም ከበሉ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ፦ ስምዖን ጴጥሮስን፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?” አለው፤ እርሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “በጎችን ጠብቅ” አለው። ዳግመኛም፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?” አለው፤ እርሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው፤ “ጠቦቶችን አሰማራ” አለው። ሦስተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?” አለው፤ ጴጥሮስም ሦስት ጊዜ ትወደኛለህን? ስላለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እኔም እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው፤ “እንኪያስ ግልገሎችን ጠብቅ” አለው። “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ አንተ ጐልማሳ ሳለህ በገዛ እጅህ ወገብህን ታጥቀህ ወደ ወደድኸው ትሄድ ነበር፤ በሸመገልህ ጊዜ ግን እጆችህን ትዘረጋለህ፤ ወገብህንም ሌላ ያስታጥቅሃል፤ ወደማትወደውም ይወስድሃል።” በምን ሞት እግዚአብሔርን ያከብር ዘንድ እንዳለው ሲያመለክት ይህን ተናገረ፤ ይህንም ብሎ ተከተለኝ አለው። ጴጥሮስም መለስ ብሎ ጌታችን ኢየሱስ ይወደው የነበረውን ያን ደቀ መዝሙር ሲከተለው አየ፤ እርሱም ራት ሲበሉ በጌታችን በኢየሱስ አጠገብ የነበረውና “ጌታ ሆይ፥ አሳልፎ የሚሰጥህ ማነው?” ያለው ነው።
የዮሐንስ ወንጌል 21 ያንብቡ
ያዳምጡ የዮሐንስ ወንጌል 21
ያጋሩ
ጌታችን ኢየሱስም፥ “እስክመጣ ይኖር ዘንድ ብወድድስ አንተን ምን አግዶህ፤ አንተ ግን ተከተለኝ” አለው። ያም ደቀ መዝሙር እንደማይሞት ይህ ነገር በወንድሞች ዘንድ ተነገረ፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን፥ “እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድድስ አንተን ምን አግዶህ” አለ እንጂ አይሞትም አላለውም። ስለዚህ ነገር ምስክር የሆነ፥ ስለ እርሱም ይህን የጻፈ ይህ ደቀ መዝሙር ነው፤ ምስክርነቱም እውነት እንደ ሆነ እኛ እናውቃለን። ጌታችን ኢየሱስ የሠራቸው ሌሎች ብዙ ሥራዎች አሉ፤ ሁሉ እያንዳንዱ ቢጻፍ ግን የተጻፉትን መጻሕፍት ዓለም ስንኳን ባልቻላቸውም ነበር። ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የዘብዴዎስ ልጅ ሐዋርያው ዮሐንስ ጌታችን በሥጋ ወደ ሰማይ ባረገ በሠላሳ ዓመት፥ ቄሳር ኔሮን በነገሠ በሰባት ዓመት በዮናናውያን ቋንቋ ለኤፌሶን ሰዎች የጻፈፍው ወንጌል ተፈጸመ። ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን። አሜን።
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የዮሐንስ ወንጌል 21:15-20, 22-25
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች