የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 20:3-10

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 20:3-10 አማ2000

ጴጥ​ሮ​ስና ያ ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙ​ርም ወጥ​ተው ወደ መቃ​ብሩ ሄዱ። ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት ሲሮጡ ያ ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙር ጴጥ​ሮ​ስን ቀድ​ሞት ወደ መቃ​ብሩ ደረሰ። ጐን​በስ ብሎም ሲመ​ለ​ከት በፍ​ታ​ዉን ተቀ​ምጦ አየ፤ ነገር ግን ወደ ውስጥ አል​ገ​ባም። ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ተከ​ት​ሎት ደረ​ሰና ወደ መቃ​ብሩ ገባ፤ በፍ​ታ​ዉ​ንም በአ​ንድ ወገን ተቀ​ምጦ አየ፤ በራሱ ላይ የነ​በ​ረው መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያም ሳይ​ቃ​ወስ ለብ​ቻው ተጠ​ቅ​ልሎ አየ፤ ከበ​ፍ​ታዉ ጋርም አል​ነ​በ​ረም። ከዚ​ህም በኋላ አስ​ቀ​ድሞ ወደ መቃ​ብሩ የደ​ረ​ሰው ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙር ገባ፤ አይ​ቶም አመነ፤ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ይነሣ ዘንድ እንደ አለው በመ​ጻ​ሕ​ፍት የተ​ጻ​ፈ​ውን ገና አላ​ወ​ቁም ነበ​ርና። ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ተመ​ል​ሰው ወደ ቤታ​ቸው ገቡ።