ጲላጦስም ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረ፤ ጽሕፈቱም፥ “የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ” የሚል ነበር። ከአይሁድም ይህቺን ጽሕፈት ያነበብዋት ብዙዎች ነበሩ፤ ጌታችን ኢየሱስን የሰቀሉበት ቦታ ለከተማ ቅርብ ነበርና፤ ጽሕፈቱም የተጻፈው በዕብራይስጥ፥ በሮማይስጥና በግሪክ ነበር። ሊቃነ ካህናትም ጲላጦስን አሉት፥ “እርሱ ራሱ ‘እኔ የአይሁድ ንጉሥ ነኝ’ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ።” ጲላጦስም፥ “የጻፍሁትን ጻፍሁ” ብሎ መለሰላቸው። ጭፍሮችም ጌታችን ኢየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው ከጭፍሮቹ ለእያንዳንዱ አራት ክፍል አድርገው መደቡት፤ ቀሚሱንም ወሰዱ፤ ቀሚሱም ከላይ ጀምሮ የተሠራ ሥረወጥ እንጂ የተሰፋ አልነበረም። እርስ በርሳቸውም፥ “ዕጣ እንጣጣልና ለደረሰ ይድረሰው እንጂ አንቅደደው ተባባሉ፤” ይህም “ልብሶችን ለራሳቸው ተካፈሉ፤ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ” ያለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው፤ ጭፍሮችም እንዲሁ አደረጉ።
የዮሐንስ ወንጌል 19 ያንብቡ
ያዳምጡ የዮሐንስ ወንጌል 19
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የዮሐንስ ወንጌል 19:19-24
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች