የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 15:18-27

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 15:18-27 አማ2000

“ዓለም ቢጠ​ላ​ችሁ አስ​ቀ​ድሞ እኔን እንደ ጠላ ዕወቁ። እና​ን​ተስ ከዓ​ለም ብት​ሆኑ ዓለም በወ​ደ​ዳ​ችሁ ነበር፤ ዓለም ወገ​ኖ​ቹን ይወ​ዳ​ልና፤ ነገር ግን እኔ ከዓ​ለም መረ​ጥ​ኋ​ችሁ እንጂ እና​ንተ ከዓ​ለም አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና ስለ​ዚህ ዓለም ይጠ​ላ​ች​ኋል። እኔ፦ ከጌ​ታው የሚ​በ​ልጥ አገ​ል​ጋይ የለም ያል​ኋ​ች​ሁን ቃሌን ዐስቡ፤ እኔን ካሳ​ደዱ እና​ን​ተ​ንም ያሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ቃሌን ጠብ​ቀው ቢሆ​ንስ ቃላ​ች​ሁ​ንም በጠ​በቁ ነበር። ነገር ግን ስለ ስሜ ይህን ሁሉ ያደ​ር​ጉ​ባ​ች​ኋል፤ የላ​ከ​ኝን አያ​ው​ቁ​ት​ምና። ባል​መ​ጣ​ሁና ባል​ነ​ገ​ር​ኋ​ቸ​ውስ ኖሮ ኀጢ​አት ባል​ሆ​ነ​ባ​ቸ​ውም ነበር፤ አሁን ግን ለኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ምክ​ን​ያት የላ​ቸ​ውም። እኔን የሚ​ጠላ አባ​ቴን ይጠ​ላል። ሌላ ያል​ሠ​ራ​ውን ሥራ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ባል​ሠራ ኖሮ ኀጢ​አት ባል​ሆ​ነ​ባ​ቸ​ውም ነበር፤ አሁን ግን እኔ​ንም አባ​ቴ​ንም አይ​ተ​ዋል፤ ጠል​ተ​ው​ማል። ነገር ግን በኦ​ሪ​ታ​ቸው፦ በከ​ንቱ ጠሉኝ ተብሎ የተ​ጻ​ፈው ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው። “እኔ ከአብ ዘንድ የም​ል​ክ​ላ​ችሁ ጰራ​ቅ​ሊ​ጦስ እር​ሱም ከአብ የሚ​ወጣ የእ​ው​ነት መን​ፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመ​ሰ​ክ​ራል። እና​ን​ተም ትመ​ሰ​ክ​ራ​ላ​ችሁ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ ከእኔ ጋር ኑራ​ች​ኋ​ልና።