ይህንም ተናግሮ ጌታችን ኢየሱስ በልቡ አዘነ፤ መሰከረ፤ እንዲህም አለ፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል።” ደቀ መዛሙርቱም ይህን ስለ ማን እንደ ተናገረ ተጠራጥረው እርስ በርሳቸው ተያዩ፤ ጌታችን ኢየሱስም ይወደው የነበረ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ በጌታችን ኢየሱስ አጠገብ ተቀምጦ ነበር። ስምዖን ጴጥሮስም እርሱን ጠቀሰና፥ “ይህን ስለ ማን እንደ ተናገረ ጠይቀህ ንገረን” አለው። ያም ደቀ መዝሙር በጌታችን ኢየሱስ አጠገብ ቀረብ ብሎ፥ “ጌታ ሆይ፥ እርሱ ማነው?” አለው። ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ይህ እኔ እንጀራ በወጥ አጥቅሼ የምሰጠው ነው” አለው፤ ያን ጊዜም እንጀራ በወጥ አጥቅሶ ለስምዖን ልጅ ለአስቆሮታዊው ይሁዳ ሰጠው። እንጀራውንም ከተቀበለ በኋላ ወዲያውኑ በይሁዳ ልብ ሰይጣን አደረበት፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “እንግዲህ የምታደርገውን ፈጥነህ አድርግ” አለው። አብረውትም በማዕድ የተቀመጡት ስለ ምን ይህን እንዳለው አላወቁም። ሙዳየ ምጽዋቱ በይሁዳ ዘንድ ነበረና፥ ለበዓል የምንሻውን ወይም ለነዳያን የምንሰጠውን ግዛ ያለው የመሰላቸው ነበሩ። ይሁዳም ያን እንጀራ ተቀብሎ ወዲያውኑ ወጣ፥ ሌሊትም ነበር።።
የዮሐንስ ወንጌል 13 ያንብቡ
ያዳምጡ የዮሐንስ ወንጌል 13
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የዮሐንስ ወንጌል 13:21-30
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች