የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 10:1-21

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 10:1-21 አማ2000

“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ በጎች ስፍራ በበሩ የማ​ይ​ገባ፥ በሌ​ላም በኩል የሚ​ገባ ሌባ፥ ወን​በ​ዴም ነው። በበሩ የሚ​ገባ ግን የበ​ጎች ጠባቂ ነው። ለእ​ርሱ በረ​ኛው ይከ​ፍ​ት​ለ​ታል፤ በጎ​ቹም ቃሉን ይሰ​ሙ​ታል፤ እር​ሱም በጎ​ቹን በየ​ስ​ማ​ቸው ይጠ​ራ​ቸ​ዋል፤ አው​ጥ​ቶም ያሰ​ማ​ራ​ቸ​ዋል። ሁሉ​ንም አው​ጥቶ ባሰ​ማ​ራ​ቸው ጊዜ በፊት በፊ​ታ​ቸው ይሄ​ዳል፤ በጎ​ቹም ይከ​ተ​ሉ​ታል፤ ቃሉን ያው​ቃ​ሉና። ሌላ​ውን ግን ይሸ​ሹ​ታል እንጂ አይ​ከ​ተ​ሉ​ትም፤ የሌ​ላ​ውን ቃሉን አያ​ው​ቁ​ምና።” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ምሳሌ ነገ​ራ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን የነ​ገ​ራ​ቸ​ውን አላ​ወ​ቁም። ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ የበ​ጎች በር እኔ ነኝ። ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦ​ችና ወን​በ​ዴ​ዎች ናቸው፤ ነገር ግን፤ በጎች አል​ሰ​ሙ​አ​ቸ​ውም። እው​ነ​ተ​ኛዉ የበ​ጎች በር እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩ​ልም የሚ​ገባ ይድ​ናል፤ ይገ​ባ​ልም ይወ​ጣ​ልም፤ መሰ​ማ​ር​ያም ያገ​ኛል። ሌባ ግን ሊሰ​ር​ቅና ሊያ​ርድ፥ ሊያ​ጠ​ፋም ካል​ሆነ በቀር አይ​መ​ጣም፤ እኔ ግን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኙ፥ እጅ​ግም እን​ዲ​በ​ዛ​ላ​ቸው መጣሁ። “ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ ነፍ​ሱን ይሰ​ጣል። ጠባቂ ያይ​ደለ፥ በጎ​ቹም ገን​ዘቡ ያይ​ደሉ ምን​ደኛ ግን፥ ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎ​ቹን ትቶ ይሸ​ሻል፤ ተኵ​ላም መጥቶ በጎ​ችን ይነ​ጥ​ቃ​ቸ​ዋል፥ ይበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ልም። ምን​ደ​ኛስ ይሸ​ሻል፤ ስለ በጎ​ችም አያ​ዝ​ንም፤ ምን​ደኛ ነውና። ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆ​ኑ​ትን መን​ጋ​ዎ​ችን አው​ቃ​ለሁ፤ የእኔ የሆ​ኑ​ትም ያው​ቁ​ኛል። አብ እኔን እን​ደ​ሚ​ያ​ው​ቀኝ እኔም አብን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ለበ​ጎ​ችም ቤዛ አድ​ርጌ ሰው​ነ​ቴን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ። ከዚህ ቦታ ያይ​ደሉ ሌሎች በጎ​ችም አሉኝ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ወደ​ዚህ አመ​ጣ​ቸው ዘንድ ይገ​ባ​ኛል፤ ቃሌ​ንም ይሰ​ሙ​ኛል፤ ለአ​ንድ እረ​ኛም አንድ መንጋ ይሆ​ናሉ። ስለ​ዚ​ህም፤ አብ ይወ​ድ​ደ​ኛል፥ እንደ ገና አስ​ነ​ሣት ዘንድ እኔ ነፍ​ሴን እሰ​ጣ​ለ​ሁና። ከእኔ ማንም አይ​ወ​ስ​ዳ​ትም፤ ነገር ግን እኔ በፈ​ቃዴ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ እኔ ላኖ​ራት ሥል​ጣን አለኝ፤ መልሼ እወ​ስ​ዳት ዘንድ ሥል​ጣን አለ​ኝና፤ ይህ​ንም ትእ​ዛዝ ከአ​ባቴ ተቀ​በ​ልሁ።” ስለ​ዚ​ህም ነገር አይ​ሁድ እን​ደ​ገና እርስ በር​ሳ​ቸው ተለ​ያዩ። ከእ​ነ​ር​ሱም ብዙ​ዎች፥ “ጋኔን ይዞት ያብ​ዳል፤ ለም​ንስ ታዳ​ም​ጡ​ታ​ላ​ችሁ?” አሉ። ሌሎ​ችም ይህ ነገር ጋኔን ከያ​ዘው ሰው የሚ​ገኝ አይ​ደ​ለም፤ ጋኔን የዕ​ዉ​ሮ​ችን ዐይን ማብ​ራት ይች​ላ​ልን?” አሉ።

Free Reading Plans and Devotionals related to የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 10:1-21