የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 5

5
የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በደል
1“በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች ሩጡ፤ ተመ​ል​ከ​ቱም፤ ዕወ​ቁም፤ በአ​ደ​ባ​ባ​ይ​ዋም ፈልጉ፤ ፍር​ድን የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን እው​ነ​ት​ንም የሚ​ሻ​ውን ሰው ታገኙ እንደ ሆነ ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 2እነ​ር​ሱም፦ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ቢሉ የሚ​ም​ሉት በሐ​ሰት ነው።” 3አቤቱ! ዐይ​ኖ​ችህ ለሃ​ይ​ማ​ኖት አይ​ደ​ሉ​ምን? አንተ ቀሥ​ፈ​ሃ​ቸ​ዋል፤ ነገር ግን አላ​ዘ​ኑም፤ ቀጥ​ቅ​ጠ​ሃ​ቸ​ው​ማል፤ ነገር ግን ተግ​ሣ​ጽን እንቢ አሉ፤ ፊታ​ቸ​ውን ከድ​ን​ጋይ ይልቅ አጠ​ን​ክ​ረ​ዋል፤ ይመ​ለ​ሱም ዘንድ እንቢ አሉ።
4እኔም እን​ዲህ አልሁ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገ​ድና የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን ፍርድ አላ​ወ​ቁ​ምና እነ​ዚህ በእ​ው​ነት ድሆ​ችና ደካ​ሞች#ዕብ. “ድሆ​ችና ሰነ​ፎች” ይላል። ናቸው፤ 5ወደ ታላ​ላ​ቆቹ እሄ​ዳ​ለሁ እና​ገ​ራ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ እነ​ርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገ​ድና የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን ፍርድ ያው​ቃ​ሉና።” እነ​ዚህ ግን ቀን​በ​ሩን በአ​ን​ድ​ነት ሰብ​ረ​ዋል፤ እስ​ራ​ቱ​ንም ቈር​ጠ​ዋል። 6ስለ​ዚህ ኀጢ​አ​ታ​ቸው በዝ​ቶ​አ​ልና፥ የዐ​መ​ፃ​ቸ​ውም ብዛት ጸን​ቶ​አ​ልና አን​በሳ ከዱር ወጥቶ ይሰ​ብ​ራ​ቸ​ዋል፤ የበ​ረ​ሃም ተኵላ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፥ ነብ​ርም በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ ይተ​ጋል፤ ከዚ​ያም የሚ​ወጣ ሁሉ ይነ​ጠ​ቃል።
7“ከእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች በየ​ት​ኛው ይቅር እል​ሻ​ለሁ? ልጆ​ችሽ ትተ​ው​ኛል፤ አማ​ል​ክ​ትም ባል​ሆኑ ምለ​ዋል፤ አጠ​ገ​ብ​ኋ​ቸ​ውም፤ እነ​ርሱ ግን አመ​ነ​ዘሩ፤ በአ​መ​ን​ዝ​ራ​ዎ​ቹም ቤት ዐደሩ። 8እንደ አለሌ ፈረ​ሶች ሆኑ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም የባ​ል​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ሚስ​ቶች አረ​ከሱ። 9በውኑ ስለ እነ​ዚህ ነገ​ሮች አል​ቀ​ሥ​ፍ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነፍ​ሴስ እን​ደ​ዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አት​በ​ቀ​ል​ምን?
10“ወደ ቅጥ​ርዋ ወጥ​ታ​ችሁ አፍ​ርሱ፤ ነገር ግን ፈጽ​ማ​ችሁ አታ​ጥፉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናቸ​ውና መጠ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋን አት​ርፉ።#ዕብ. “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ሉ​ምና ቅር​ን​ጫ​ፍ​ዋን ውሰዱ” ይላል። 11የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና የይ​ሁዳ ቤት በእኔ ላይ እጅግ ወን​ጅ​ለ​ዋል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 12የይ​ሁ​ዳም ወገ​ኖች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዋሹ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ክፉ ነገ​ርም አይ​መ​ጣ​ብ​ንም ሰይ​ፍ​ንና ራብ​ንም አና​ይም፤ 13ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ችን ነፋስ ናቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በእ​ነ​ርሱ ዘንድ የለም፤ እን​ዲ​ህም ይደ​ረ​ግ​ባ​ቸ​ዋል።”
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን እን​ደ​ተ​ዋ​ቸው
14ስለ​ዚ​ህም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እን​ደ​ዚህ ያለ ቃል ተና​ግ​ራ​ች​ኋ​ልና እነሆ በአ​ፍህ ውስጥ ቃሌን እሳት፥ ይህ​ንም ሕዝብ እን​ጨት አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ትበ​ላ​ቸ​ው​ማ​ለች። 15የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እነሆ ሕዝ​ብን ከሩቅ አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ኀያል ጥን​ታዊ ሕዝብ ነው፤#“ኀያል ጥን​ታዊ ሕዝብ ነው” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ቋን​ቋ​ቸ​ው​ንም የማ​ታ​ው​ቀው፥ የሚ​ና​ገ​ሩ​ት​ንም የማ​ታ​ስ​ተ​ው​ለው ሕዝብ ነው። 16#ዕብ. “የፍ​ላ​ጻ​ቸው ሰገባ” ይላል።ከን​ፈ​ራ​ቸ​ውም እንደ ተከ​ፈተ መቃ​ብር ነው፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከን​ፈ​ራ​ቸው እንደ ተከ​ፈተ መቃ​ብር ነው”አይ​ልም። ሁሉም ኀያ​ላን ናቸው። 17መከ​ር​ህ​ንና እን​ጀ​ራ​ህን ይበ​ላሉ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ህ​ንም ይበ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ በጎ​ች​ህ​ንና ላሞ​ች​ህ​ንም ይበ​ላሉ፤ ወይ​ን​ህ​ንና በለ​ስ​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም ይበ​ላሉ፤ የም​ት​ታ​መ​ና​ቸ​ውን የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ች​ህ​ንም በሰ​ይፍ ያጠ​ፋሉ።” 18ነገር ግን “በዚያ ዘመን ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ች​ሁም።”
19እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እና​ንተ፥ “አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለ ምን አደ​ረ​ገ​ብን?” ብትሉ፥ አንተ፥ “እንደ ተዋ​ች​ሁኝ፥ በሀ​ገ​ራ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት እን​ዳ​መ​ለ​ካ​ችሁ፥ እን​ዲሁ ለእ​ና​ንተ ባል​ሆነ ሀገር ለሌ​ሎች ሰዎች ትገ​ዛ​ላ​ችሁ” ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን እን​ዳ​ስ​ጠ​ነ​ቀቀ
20ይህ​ንም በያ​ዕ​ቆብ ቤት አውሩ፤ በይ​ሁ​ዳም አሰሙ፦ 21እና​ንተ ሰነ​ፎች ልበ ቢሶች፥ ዐይን እያ​ላ​ችሁ የማ​ታዩ፥ ጆሮም እያ​ላ​ችሁ የማ​ት​ሰሙ ሕዝብ ሆይ! ይህን ስሙ። 22በውኑ እኔን አት​ፈ​ሩ​ምን? ከፊ​ቴስ አት​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ዳ​ያ​ልፍ አሸ​ዋን በዘ​ለ​ዓ​ለም ትእ​ዛዝ ለባ​ሕር ዳርቻ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ሞገ​ዱም ቢት​ረ​ፈ​ረ​ፍና ቢጮኽ ከእ​ርሱ አያ​ል​ፍም።
23ለዚ​ህም ሕዝብ የማ​ይ​ሰ​ማና የዐ​መፀ ልብ አላ​ቸው፤ ተመ​ል​ሰ​ውም ሄደ​ዋል። 24በል​ባ​ቸ​ውም፦ የመ​ከ​ሩ​ንና የበ​ል​ጉን ዝናብ በጊዜ የሚ​ሰ​ጠ​ውን፥ ለመ​ከ​ርም የተ​መ​ደ​ቡ​ትን ወራት የሚ​ጠ​ብ​ቅ​ል​ንን አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ፍራ አላ​ሉም። 25በደ​ላ​ች​ሁም እነ​ዚ​ህን አስ​ቀ​ር​ታ​ለች፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም መል​ካ​ምን ነገር ከእ​ና​ንተ አር​ቃ​ለች። 26በሕ​ዝቤ መካ​ከል ክፉ​ዎች ሰዎች ተገ​ኝ​ተ​ዋል፤ ሰዎ​ች​ንም ይዘው ይገ​ድሉ ዘንድ ወጥ​መ​ድን ይዘ​ረ​ጋሉ። 27ቀፎ ወፎ​ችን እን​ደ​ሚ​ሞላ፥ እን​ዲሁ ቤታ​ቸው ሽን​ገ​ላን ሞል​ታ​ለች፤ በዚ​ህም ከብ​ረ​ዋል ባለ​ጸ​ጎ​ችም ሆነ​ዋል። 28ፍር​ድን አጣ​መሙ ለድ​ሃ​አ​ደ​ጎች ፍር​ድን አል​ፈ​ረ​ዱም፤ ለመ​በ​ለ​ቷም አል​ተ​ሟ​ገ​ቱም።#ዕብ. “ወፍ​ረ​ዋል ፤ ሰብ​ተ​ው​ማል ፤ ክፋ​ታ​ቸ​ው​ንም ያለ ልክ አብ​ዝ​ተ​ዋል ፤ የደሀ አደ​ጎች ነገር መል​ካም እን​ዲ​ሆን አል​ተ​ም​ዋ​ገ​ቱ​ላ​ቸ​ውም ፤ የች​ግ​ረ​ኞ​ች​ንም ፍርድ አል​ፈ​ረ​ዱ​ላ​ቸ​ውም” ይላል። 29በውኑ ስለ እነ​ዚህ ነገ​ሮች አል​ቀ​ሥ​ፍ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነፍ​ሴስ እን​ደ​ዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አት​በ​ቀ​ል​ምን?
30የም​ት​ሰ​ቀ​ጥ​ጥና የም​ታ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ነገር በም​ድር ላይ ሆና​ለች፤ 31ነቢ​ያት በሐ​ሰት ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ፥ ካህ​ና​ትም በእ​ጃ​ቸው ያጨ​በ​ጭ​ባሉ፥#ዕብ. “በእ​ነ​ዚህ እጅ ይገ​ዛሉ” ይላል። ሕዝ​ቤም እን​ዲህ ያለ​ውን ነገር ይወ​ድ​ዳሉ፤ በፍ​ጻ​ሜ​ውስ ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ