የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 30

30
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ የሰ​ጠው ተስፋ
1ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው ቃል ይህ ነው። እን​ዲ​ህም አለው፤ 2“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የነ​ገ​ር​ሁ​ህን ቃል ሁሉ በመ​ጽ​ሐፍ ጻፍ። 3እነሆ! የሕ​ዝ​ቤን የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንና የይ​ሁ​ዳን ምርኮ የም​መ​ል​ስ​በት ዘመን ይመ​ጣ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ሰጠ​ኋት ምድር እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይገ​ዙ​አ​ታል።”
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ላይ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “የሚ​ያ​ስ​ፈራ ድምፅ ትሰ​ማ​ላ​ችሁ፤ ፍር​ሀት ነው እንጂ ሰላም አይ​ደ​ለም። 6ጠይቁ፤ ወንድ ይወ​ልድ እንደ ሆነ ተመ​ል​ከቱ፤ ስለ ምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ እጁን በወ​ገቡ ላይ አድ​ርጎ፥ ፊቱም ሁሉ ወደ ጥቍ​ረት ተለ​ውጦ አየሁ? 7ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ነውና፥ እር​ሱ​ንም የሚ​መ​ስል የለ​ምና፤ ያ የያ​ዕ​ቆብ መከራ ዘመን ነው፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ይድ​ናል። 8በዚያ ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ቀን​በ​ርን ከአ​ን​ገ​ትህ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ እስ​ራ​ት​ህ​ንም እበ​ጥ​ሳ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ለሌላ አት​ገ​ዛም። 9ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ ለማ​ስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው ለን​ጉ​ሣ​ቸው ለዳ​ዊ​ትም ይገ​ዛሉ።
10“እነሆ አን​ተን ከሩቅ፥ ዘር​ህ​ንም ከም​ርኮ ሀገር አድ​ና​ለ​ሁና ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ ሆይ! አት​ፍራ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተም እስ​ራ​ኤል ሆይ! አት​ደ​ን​ግጥ፤ ያዕ​ቆ​ብም ይመ​ለ​ሳል፤ ያር​ፍ​ማል፤ ተዘ​ል​ሎም ይቀ​መ​ጣል፤ ማንም አያ​ስ​ፈ​ራ​ውም። 11አድ​ንህ ዘንድ ከአ​ንተ ጋር ነኝና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተ​ንም የበ​ተ​ን​ሁ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለሁ፤ አን​ተን ግን ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ህም፤ በመ​ጠን እቀ​ጣ​ሃ​ለሁ፥” ያለ ቅጣ​ትም ከቶ አል​ተ​ው​ህም።”#ምዕ. 30 ቍ. 10 እና 11 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ስብ​ራ​ትህ የማ​ይ​ፈ​ወስ፥ ቍስ​ል​ህም ክፉ ነው። 13ትጠ​ገን ዘንድ ክር​ክ​ር​ህን የሚ​ፈ​ር​ድ​ልህ ሰው የለም፤ ቍስ​ል​ህ​ንም የሚ​ፈ​ውስ መድ​ኀ​ኒት የለ​ህም። 14ወዳ​ጆ​ችህ ሁሉ ረስ​ተ​ው​ሃል፤ አይ​ፈ​ል​ጉ​ህ​ምም፤ በደ​ልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢ​አ​ት​ህም ስለ በዛ፥ በጠ​ላት ማቍ​ሰ​ልና በጨ​ካኝ ቅጣት አቍ​ስ​ዬ​ሃ​ለ​ሁና። 15ቍስ​ልህ የማ​ይ​ፈ​ወስ ሆኖ​አ​ልና ስለ ስብ​ራ​ትህ ለምን ትጮ​ኻ​ለህ? በደ​ልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢ​አ​ት​ህም ስለ በዛ፥ ይህን አድ​ር​ጌ​ብ​ሃ​ለሁ። 16ስለ​ዚህ የሚ​በ​ሉህ ሁሉ ይበ​ላሉ፤ የሚ​ማ​ር​ኩ​ህም ሁላ​ቸው ይማ​ረ​ካሉ፤ የዘ​ረ​ፉ​ህም ይዘ​ረ​ፋሉ፤ የሚ​ማ​ር​ኩ​ህ​ንም ሁሉ ለመ​ማ​ረክ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ።#ምዕ. 30 ቁ. 15 እና 16 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም ተዘ​ዋ​ው​ሮ​አል። 17እኔ ከክፉ ቍስ​ልሽ እፈ​ው​ስ​ሻ​ለሁ፤ ጤና​ሽን እመ​ል​ስ​ል​ሻ​ለሁ፤ ቍስ​ል​ሽ​ንም እፈ​ው​ሳ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ማንም የማ​ይ​ሻት፥ የተ​ጣ​ለች ጽዮን ብለው ጠር​ተ​ው​ሻ​ልና።”
18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ የያ​ዕ​ቆ​ብን ድን​ኳን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለማ​ደ​ሪ​ያ​ውም እራ​ራ​ለሁ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም በጕ​ብ​ታዋ ላይ ትሠ​ራ​ለች፤ አዳ​ራ​ሹም እንደ ዱሮው የሰው መኖ​ሪያ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሕዝ​ቡም እን​ደ​የ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ” ይላል። ይሆ​ናል። 19ከእ​ር​ሱም ዘንድ የም​ስ​ጋ​ናና የዘ​ፈን ድምፅ ይወ​ጣል፤ እኔም አበ​ዛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አያ​ን​ሱ​ምም። 20ልጆ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ቀድ​ሞው ይሆ​ናሉ፤ ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም#ዕብ. “ማኅ​በ​ራ​ቸ​ውም” ይላል። በፊቴ ጸንቶ ይኖ​ራል፤ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ቸ​ው​ንም ሁሉ እቀ​ጣ​ለሁ። 21አለ​ቃ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ውስጥ ይሾ​ማል፤ ገዢ​አ​ቸ​ውም ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ይወ​ጣል፤ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እኔም እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እኔ ይመ​ለስ ዘንድ ልብ የሰ​ጠው ማን ነው? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 22እና​ን​ተም ሕዝብ ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ።”#ምዕ. 30 ቍ. 22 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
23እነሆ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ለመ​ቅ​ሠ​ፍት ወጥ​ቶ​አል፤ የመ​ዓ​ቱ​ንም ጥፋት በኃ​ጥ​ኣን ራስ ላይ አም​ጥ​ቶ​አል፤ 24የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ የል​ቡን አሳብ ሠርቶ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ አይ​መ​ለ​ስም፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን ታው​ቁ​ታ​ላ​ችሁ።#ምዕ. 30 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 37 ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ