የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 28

28
ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስና ሐሰ​ተ​ኛው ነቢይ ሐና​ንያ
1ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ በዚያ ዓመት፥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ መን​ግ​ሥት መጀ​መ​ሪያ፥ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ሐሰ​ተ​ኛው#“ሐሰ​ተ​ኛው” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ነቢይ የገ​ባ​ዖን ሰው የዓ​ዙር ልጅ ሐና​ንያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በካ​ህ​ና​ትና በሕ​ዝብ ሁሉ ፊት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረኝ፦ 2“የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አለ፦ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ቀን​በር ሰብ​ሬ​አ​ለሁ። 3የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከዚች ስፍራ ወደ ባቢ​ሎን የወ​ሰ​ዳ​ቸ​ውን#“ከዚች ስፍራ ወደ ባቢ​ሎን የወ​ሰ​ዳ​ቸ​ውን” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ​ዎች ሁሉ በሁ​ለት ዓመት ውስጥ ወደ​ዚ​ህች ስፍራ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ 4ወደ ባቢ​ሎ​ንም የሄ​ዱ​ትን የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ልጅ#“ወደ ባቢ​ሎ​ንም የሄ​ዱ​ትን የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ልጅ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ኢኮ​ን​ያ​ን​ንና የይ​ሁ​ዳን ምርኮ ሁሉ ወደ​ዚች ስፍራ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ቀን​በር እሰ​ብ​ራ​ለ​ሁና።”
5ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም በካ​ህ​ና​ቱና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በቆ​ሙት ሕዝብ ሁሉ ፊት ለሐ​ሰ​ተ​ኛው ነቢይ ለሐ​ና​ንያ ተና​ገረ። 6ነቢ​ዩም ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ አለ፥ “አሜን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያድ​ርግ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ፥ ምር​ኮ​ው​ንም ሁሉ ከባ​ቢ​ሎን ወደ​ዚህ ስፍራ በመ​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ትን​ቢት ይፈ​ጽም። 7ነገር ግን በጆ​ሮ​ህና በሕ​ዝቡ ሁሉ ጆሮ የም​ና​ገ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ 8ከጥ​ንት ከእ​ኔና ከአ​ንተ በፊት የነ​በሩ ነቢ​ያት በብዙ ሀገ​ርና በታ​ላ​ላቅ መን​ግ​ሥ​ታት ላይ ስለ ሰል​ፍና ስለ ክፉ ነገር ስለ ቸነ​ፈ​ርም#“ስለ ክፉ ነገር ስለ ቸነ​ፈ​ርም” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ትን​ቢት ተና​ገሩ። 9ስለ ሰላም ትን​ቢት የተ​ና​ገረ ነቢይ ትን​ቢቱ በደ​ረሰ ጊዜ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ው​ነት የላ​ከው ነቢይ እንደ ሆነ ይታ​ወ​ቃል።”
10ሐሰ​ተ​ኛው ነቢይ ሐና​ን​ያም በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት ቀን​በ​ሩን ከነ​ቢዩ ከኤ​ር​ም​ያስ አን​ገት ወስዶ ሰበ​ረው። 11ሐና​ን​ያም በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እን​ግ​ዲህ በሁ​ለት ዓመት ውስጥ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ የና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን ቀን​በር ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ አን​ገት እሰ​ብ​ራ​ለሁ” አለ። ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም መን​ገ​ዱን ሄደ።
12ሐና​ን​ያም ቀን​በ​ሩን ከነ​ቢዩ ኤር​ም​ያስ አን​ገት ከሰ​በረ በኋላ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 13“ሂድ፥ ለሐ​ና​ንያ እን​ዲህ ብለህ ንገ​ረው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አንተ የእ​ን​ጨ​ትን ቀን​በር ሰብ​ረ​ሃል፤ እኔ ግን በእ​ርሱ ፋንታ የብ​ረ​ትን ቀን​በር እሠ​ራ​ለሁ። 14የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ይገ​ዙ​ለት ዘንድ የብ​ረ​ትን ቀን​በር በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ አን​ገት ላይ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይገ​ዙ​ለ​ታል፤ የም​ድረ በዳ አራ​ዊ​ትን ደግሞ ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።”#“እነ​ር​ሱም ይገ​ዙ​ለ​ታል የም​ድረ በዳ አራ​ዊ​ትን ደግሞ ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 15ነቢ​ዩም ኤር​ም​ያስ ሐሰ​ተ​ኛ​ውን ሐና​ን​ያን፥ “ሐና​ንያ ሆይ ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ላ​ከ​ህም፤ ነገር ግን ይህ ሕዝብ በሐ​ሰት እን​ዲ​ታ​መን አድ​ር​ገ​ሃል። 16ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ከገጸ ምድር አስ​ወ​ግ​ድ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐመ​ፅን ተና​ግ​ረ​ሃ​ልና#“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዓመ​ፅን ተና​ግ​ረ​ሃ​ልና” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በዚህ ዓመት ትሞ​ታ​ለህ” አለው። 17ሐሰ​ተ​ኛው ነቢይ ሐና​ን​ያም በዚ​ያው ዓመት በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ሞተ።#ምዕ. 28 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 35 ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ