የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 22

22
የኤ​ር​ም​ያስ መል​እ​ክት ለይ​ሁዳ ቤተ መን​ግ​ሥት
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ውረድ፤ በዚ​ያም ይህን ቃል ተና​ገር፥ እን​ዲ​ህም በል፦ 2በዳ​ዊት ዙፋን የም​ት​ቀ​መጥ የይ​ሁዳ ንጉሥ ሆይ! አን​ተና አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቤትህ” ይላል። በእ​ነ​ዚ​ህም በሮች የሚ​ገባ ሕዝ​ብህ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን አድ​ርጉ፤ የተ​ነ​ጠ​ቀ​ው​ንም ከአ​ስ​ጨ​ና​ቂው እጅ አድኑ፤ መጻ​ተ​ኛ​ው​ንና ድሃ​አ​ደ​ጉን፥ ባል​ቴ​ቲ​ቱ​ንም አት​በ​ድሉ፤ አታ​ም​ፁ​ባ​ቸ​ውም፤ በዚ​ህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታ​ፍ​ስሱ። 4ይህ​ንም ነገር ብታ​ደ​ርጉ፥ በዳ​ዊት ዙፋን የሚ​ቀ​መጡ ነገ​ሥ​ታት በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና በፈ​ረ​ሶች ላይ ተቀ​ም​ጠው፥ በዚህ ቤት በሮች ይገ​ባሉ፤ እነ​ር​ሱም፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም፥ ሕዝ​ቡም እን​ዲሁ ይገ​ባሉ። 5ነገር ግን ይህን ቃል ባት​ሰሙ፥ ይህ ቤት ወና እን​ዲ​ሆን በራሴ ምያ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለ​ዓ​ድና እንደ ሊባ​ኖስ ራስ ነህ፤ በር​ግጥ ምድረ በዳና ማንም የማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው ከተ​ሞች አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ። 7የሚ​አ​ጠ​ፋ​ህን ሰው በአ​ንተ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ም​ረ​ውን ዛፍ​ህ​ንም በም​ሳር ይቈ​ር​ጣል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ላል። 8ብዙ አሕ​ዛ​ብም በዚች ከተማ ላይ ያል​ፋሉ፤ ሁሉም ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚች ታላቅ ከተማ ለምን እን​ዲህ አደ​ረገ? ይላሉ። 9እነ​ር​ሱም፦ የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ትተው ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት ስለ ሰገዱ፥ ስለ አመ​ለ​ኳ​ቸ​ውም ነው ብለው ይመ​ል​ሳሉ።”
10ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​መ​ለ​ስ​ምና፥ የተ​ወ​ለ​ደ​ባ​ት​ንም ሀገር አያ​ይ​ምና ለሚ​ወጣ እጅግ አል​ቅሱ እንጂ ለሞተ አታ​ል​ቅሱ፤ አት​ዘ​ኑ​ለ​ትም። 11በአ​ባቱ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ፋንታ ስለ ነገ​ሠው፥ ከዚ​ህም ስፍራ ስለ ወጣ​ውና ስለ​ማ​ይ​መ​ለ​ሰው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮ​ስ​ያስ ልጅ፥ ስለ ሳሌም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ 12“በተ​ማ​ረ​ከ​በት ሀገር ይሞ​ታል፤ እን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ሀገ​ሩን አያ​ይም።”
13ቤቱን በዐ​መፅ፥ አዳ​ራ​ሹ​ንም ያለ እው​ነት ለሚ​ሠራ፥ ባል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም እን​ዲ​ያው በከ​ንቱ ለሚ​ያ​ሠራ፥ ዋጋ​ው​ንም ለማ​ይ​ሰ​ጠው ወዮ​ለት! 14“ለራሴ ሰፊ ቤት፥ ትል​ቅም ሰገ​ነት እሠ​ራ​ለሁ ለሚል፥ መስ​ኮ​ት​ንም ለሚ​ያ​ወጣ፥ በዝ​ግ​ባም ሥራ ለሚ​ያ​ስ​ጌጥ፥ በቀይ ቀለ​ምም ለሚ​ቀ​ባው ወዮ​ለት፤ 15በአ​ባ​ትህ ዝግባ አዳ​ራሽ ስለ ሠራህ በውኑ ትነ​ግ​ሣ​ለ​ህን? በውኑ አባ​ትህ አይ​በ​ላና አይ​ጠ​ጣም ነበ​ርን? ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅ​ንስ አያ​ደ​ር​ግም ነበ​ርን? በዚ​ያም ጊዜ መል​ካም ሆኖ​ለት ነበር።#ምዕ. 22 ቁ. 15 ዕብ​ራ​ይ​ስጥ፥ ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ግእዝ አይ​ገ​ና​ኙም። 16የድ​ሃ​ው​ንና የች​ግ​ረ​ኛ​ውን ፍርድ ይፈ​ርድ ነበር፤ በዚ​ያም ጊዜ መል​ካም ሆኖ ነበር። ይህ እኔን ማወቅ አይ​ደ​ለ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 17እነሆ ዐይ​ን​ህና ልብህ መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ለቅ​ሚያ፥ ንጹሕ ደም​ንም ለማ​ፍ​ሰስ፥ ግድ​ያ​ንና ግፍ​ንም ለመ​ሥ​ራት ብቻ ነው።” 18ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮ​ስ​ያስ ልጅ ስለ ኢዮ​አ​ቄም እን​ዲህ ይላል፥ “ወን​ድሜ ሆይ፥ ወዮ! ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! እያለ የሚ​ያ​ለ​ቅ​ስ​ለት ለሌ​ለው ለዚያ ሰው ወዮ​ለት! 19አህ​ያም#ግእዝ “መቃ​ብረ መሪረ” ይላል። እን​ደ​ሚ​ቀ​በር ይቀ​በ​ራል፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በር ወደ ውጭ ተጐ​ትቶ፥ በው​ራጅ ጨርቅ ተጠ​ቅ​ልሎ#“በው​ራጅ ጨርቅ ተጠ​ቅ​ልሎ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ይጣ​ላል።”
20ወዳ​ጆ​ችሽ ሁሉ ጠፍ​ተ​ዋ​ልና ወደ ሊባ​ኖስ ወጥ​ተሽ ጩኺ፤ በባ​ሳ​ንም ላይ ድም​ፅ​ሽን አንሺ፤ በባ​ሕ​ሩም ማዶ ጩኺ። 21በጐ​ሰ​ቈ​ልሽ#ዕብ. “በደ​ኅ​ን​ነ​ትሽ” ይላል። ጊዜ ተና​ገ​ር​ሁሽ፤ አን​ቺም፦ አል​ሰ​ማም አልሽ፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትሽ ጀምሮ ቃሌን አለ​መ​ስ​ማ​ትሽ መን​ገ​ድሽ ነው። 22በግ#“በግ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ሽን ሁሉ ነፋስ ይወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋል፤ ወዳ​ጆ​ች​ሽም ተማ​ር​ከው ይሄ​ዳሉ፤ በዚ​ያን ጊዜም ስለ ክፋ​ትሽ ሁሉ ታፍ​ሪ​ያ​ለሽ፤ በወ​ዳ​ጆ​ች​ሽም ፊት ቷረ​ጃ​ለሽ። 23አንቺ በሊ​ባ​ኖስ የም​ት​ቀ​መጪ፥ በዝ​ግባ ዛፍም ውስጥ የም​ታ​ለ​ቅሺ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያ​ዘሽ ጊዜ እን​ዴት ትጨ​ነ​ቂ​ያ​ለሽ!
በኢ​ዮ​አ​ቄም ላይ የደ​ረሰ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ
24“እኔ ሕያው ነኝ የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄም ልጅ ኢኮ​ን​ያን ሆይ፥ አን​ተን በሰ​ወ​ር​ሁ​በት ቀኝ እጄ እን​ዳለ ማሕ​ተም ነበ​ርህ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ግን እን​ደ​ማ​ት​ኖር እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ 25ነፍ​ስ​ህ​ንም ለሚ​ሹ​አት፥ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ለም​ት​ፈ​ራ​ቸው እጅ፥ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርና ለከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም እጅ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ። 26አን​ተ​ንም፥ የወ​ለ​ደ​ች​ህን እና​ት​ህ​ንም ወዳ​ል​ተ​ወ​ለ​ዳ​ች​ሁ​ባት ወደ ሌላ ሀገር እጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ። 27ነፍ​ሳ​ች​ሁም ወደ​ም​ት​መ​ኛት ወደ​ዚ​ያች ምድር አት​መ​ለ​ሱም። 28ኢኮ​ን​ያን ተዋ​ረደ፤ ለም​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ቅም የሸ​ክላ ዕቃ ሆነ፤ እር​ሱ​ንና ዘሩን ወደ​ማ​ያ​ው​ቀው ሀገር ወር​ው​ረው ጥለ​ው​ታ​ልና። 29ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሚ። 30እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዘ​መኑ አይ​ከ​ና​ወ​ን​ምና፥ ከዘ​ሩም በዳ​ዊት ዙፋን የሚ​ቀ​መጥ አይ​ነ​ሣ​ምና፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ለይ​ሁዳ ገዢ አይ​ሾ​ም​ምና ይህን ሰው እንደ ሞተ ቍጠ​ሪው” አለ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ