ጌዴዎንም ሕልሙንና ትርጓሜዉን በሰማ ጊዜ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ ወደ እስራኤልም ሰፈር ተመልሶ፥ “እግዚአብሔር የምድያምን ሠራዊት በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና ተነሡ” አለ። ሦስቱንም መቶ ሰዎች በሦስት ወገን ከፈላቸው፤ በሁሉም እጅ ቀንደ መለከትና ባዶ ማሰሮ፥ በማሰሮዉም ውስጥ ችቦ ሰጣቸው። እርሱም፥ “እኔን ተመልከቱ፤ እንዲሁም አድርጉ፤ እነሆም፥ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ በደረስሁ ጊዜ እኔ እንደማደርግ እንዲሁ እናንተ አድርጉ፤ እኔ ከእኔም ጋር ያሉት ሁሉ ቀንደ መለከት ስንነፋ፥ እናንተ ደግሞ በሰፈሩ ዙሪያ ሁሉ ቀንደ መለከታችሁን ንፉ፦ ኀይል የእግዚአብሔር፥ ሰይፍ የጌዴዎን በሉ” አላቸው። ጌዴዎንም፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት መቶ ሰዎች በመካከለኛው ትጋት መጀመሪያ ዘብ ጠባቂዎች ሳይነቁ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ ቀንደ መለከቶችንም ነፉ፤ በእጃቸውም የነበሩትን ማሰሮዎች ሰባበሩ፤ ሦስቱም ወገኖች ቀንደ መለከቶችን ነፉ፤ ማሰሮዎችንም ሰበሩ፤ በግራ እጃቸውም ችቦዎችን፥ በቀኝ እጃቸውም ቀንደ መለከቶችን ይዘው እየነፉ፥ “የእግዚአብሔርና የጌዴዎን ሰይፍ” ብለው ጮኹ። ሁሉም በየቦታው፥ በሰፈሩ ዙሪያ ቆመ፤ ሠራዊቱም ሁሉ ደንግጠው ሸሹ። ሦስቱንም መቶ ቀንደ መለከቶችን ነፉ፤ እግዚአብሔርም የሰውን ሁሉ ሰይፍ በባልንጀራዉና በሠራዊቱ ሁሉ ላይ አደረገ፤ ሠራዊቱም በጽሬራ በኩል እስከ ቤትሲጣ ጋራጋታ ድረስ በጣባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልሜሁላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ። የእስራኤልም ሰዎች ከንፍታሌምና ከአሴር፥ ከምናሴም ሁሉ ተሰብስበው ምድያምን አሳደዱ።
መጽሐፈ መሳፍንት 7 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መሳፍንት 7:15-23
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች