እርሱም፥ “እግዚአብሔር አምላክ ጠላቶቻችንን ሞዓባውያንን በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናልና ተከተሉኝ” አላቸው። ተከትለውትም ወረዱ፤ ወደ ሞዓብም የሚያሻግረውን የዮርዳኖስን መሻገርያ ያዙ፤ ማንም ሰው እንዲያልፍ አልፈቀዱም። በዚያም ወራት ከሞዓብ ዐሥር ሺህ የሚያህሉትን፥ ጐልማሶችና ጽኑዓን ሁሉ ገደሉ፤ ከእነርሱም አንድ ሰው እንኳ አላመለጠም። በዚያም ወራት ሞዓባውያን በእስራኤል እጅ ገቡ፤ ምድሪቱም ሰማንያ ዓመት ዐረፈች። ናዖድም እስኪሞት ድረስ ገዛቸው። ከእርሱም በኋላ የሐናት ልጅ ሴሜጋር ተነሣ፤ ከፍልስጥኤማውያንም ስድስት መቶ ሰው በበሬ መውጊያ ገደለ፤ እርሱም ደግሞ እስራኤልን አዳነ።
መጽሐፈ መሳፍንት 3 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መሳፍንት 3:28-31
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች